Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 13:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እና​ንተ ‘መም​ህ​ራ​ችን፥ ጌታ​ች​ንም’ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ፤ መል​ካም ትላ​ላ​ችሁ፤ እኔ እን​ዲሁ ነኝና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እናንተ፣ ‘መምህርና፣ ጌታ’ ትሉኛላችሁ፤ ትክክል ነው፤ እንደምትሉኝ እንዲሁ ነኝና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ ስለሆንኩም መልካም ትናገራላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እናንተ ‘መምህርና ጌታ’ ትሉኛላችሁ፤ እኔ መምህርና ጌታ ስለ ሆንኩ ያላችሁት ትክክል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 13:13
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን እፈ​ጽ​መው ዘንድ እተ​ጋ​ለ​ሁና መል​ካም አይ​ተ​ሃል” አለኝ።


እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “መል​ካም መል​ሰ​ሃል፤ እን​ዲሁ አድ​ርግ፤ ትድ​ና​ለ​ህም” አለው።


“ለምን አቤቱ፥ አቤቱ፥ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ? የም​ላ​ች​ሁ​ንም አታ​ደ​ር​ጉም።


ስም​ዖ​ንም መልሶ፥ “ብዙ​ውን የተ​ወ​ለት ነው እላ​ለሁ” አለው፤ እር​ሱም፥ “መል​ካም ፈረ​ድህ” አለው።


ማር​ያም ግን ጌታ​ች​ንን ሽቱ የቀ​ባ​ችው፥ እግ​ሩ​ንም በጠ​ጕ​ርዋ ያሸ​ችው ናት፤ ወን​ድ​ምዋ አል​ዓ​ዛ​ርም ታሞ ነበር።


ይህ​ንም ብላ ሄደች፤ እኅ​ቷን ማር​ያ​ም​ንም ቀስ ብላ ጠራ​ችና፥ “እነሆ፥ መም​ህ​ራ​ችን መጥቶ ይጠ​ራ​ሻል” አለ​ቻት።


እኅ​ቶ​ቹም፥ “ጌታ​ችን ሆይ፥ እነሆ፥ የም​ት​ወ​ደው ታሞ​አል” ብለው ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ላኩ።


ስለ​ዚ​ህም ማንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ሲና​ገር፥ “ኢየ​ሱስ ውጉዝ ነው” የሚል እን​ደ​ሌለ፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ካል​ሆነ በቀር “ኢየ​ሱስ ጌታ ነው” ሊል አን​ድስ እን​ኳን እን​ዳ​ይ​ችል አስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።


ለእ​ኛስ ሁሉ ከእ​ርሱ የሆነ፥ እኛም ለእ​ርሱ የሆን አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ አለን፤ ሁሉ በእ​ርሱ የሆነ፥ እኛም በእ​ርሱ የሆን አንድ ጌታ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም አለን።


እና​ን​ተም ጌቶች ሆይ፥ ቍጣ​ች​ሁን እያ​በ​ረ​ዳ​ችሁ፥ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ይቅር እያ​ላ​ችሁ፥ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ ፊት አይቶ የማ​ያ​ዳላ ጌታ በእ​ነ​ር​ሱና በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ማይ እንደ አለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


አን​ደ​በ​ትም ሁሉ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ ክብር ጌታ እንደ ሆነ ያምን ዘንድ ነው።


ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግ​ለው ዘንድ፥ ሁሉን የተ​ው​ሁ​ለት፥ እንደ ጕድ​ፍም ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት የጌ​ታ​ዬን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ኀይ​ልና ገና​ና​ነት ስለ​ማ​ውቅ ሁሉን እንደ ኢም​ንት ቈጠ​ር​ሁት።


እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ፤ ይንቀጠቀጡማል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች