ኤርምያስ 39:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ወደ እርሱም ኮብልለው የነበሩትን ሰዎች፥ የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማርኮ አፈለሳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን መንግሥት የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዛርዳን በከተማ የቀሩትን ሕዝብና ቀደም ብለው ወደ እርሱ ከድተው የገቡትንም ሁሉ በአንድነት ሰብስቦ በእስረኛነት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ኰብልለውም ወደ እርሱ የገቡትን ሰዎችና የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ የቀሩትን ሕዝብ ወደ እርሱም የኰበለሉትን ሰዎች የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው። |
ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን አጋዛቸው፤
ስለዚህ ከዚህች ምድር እናንተና አባቶቻችሁ ወዳላወቃችኋት ምድር እጥላችኋለሁ፤ ምሕረትንም አላደርግላችሁምና በዚያ ሌሎችን አማልክት ቀንና ሌሊት ታገለግላላችሁ።’
“ነገር ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ከክፋቱ የተነሣ ሊበላ እንደማይችል እንደ ክፉው በለስ፥ እንዲሁ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን አለቆቹንም፥ በዚህችም አገር የሚቀሩትን የኢየሩሳሌምን ትሩፍ፥ በግብጽም አገር የሚቀመጡትን ክፉውን አደርግባቸዋለሁ።
ወደ ባቢሎን በተማረኩት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ መካከል የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን እርሱን በሰንሰለት አስሮ በመውሰድ ከራማ ከለቀቀው በኋላ፥ ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
በየሜዳውም የነበሩት የጭፍራ አለቆችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድሪቱ ላይ እንደ ሾመ፥ ወንዶችንና ሴቶችን ሕፃናትንም፥ ወደ ባቢሎን ያልተማረኩትን በምድሪቱ ያሉትን ድሆች፥ እንዲገዛ ኀላፊነት እንደሰጠው በሰሙ ጊዜ፥