ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፥ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ ጌታ ገነት በግብጽ ምድር አምሳል ነበረ።
ዘፍጥረት 13:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎጥም በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን አገር ሁሉ መረጠ፥ ሎጥም ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፥ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተለያዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሎጥ የዮርዳኖስን ረባዳ ሜዳ በሙሉ መርጦ ወደ ምሥራቅ አመራ፤ ሁለቱ ሰዎች በዚሁ ተለያዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሎጥ መላውን የዮርዳኖስን ሸለቆ ለራሱ መረጠና ወደ ምሥራቅ ሄደ፤ ሁለቱ የተለያዩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎጥም ለራሱ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን ሀገር ሁሉ መረጠ፤ ሎጥም ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፤ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተለያዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎጥም በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን አገር ሁሉ መረጠ ሎጥም ወደ ምሥርቅ ተጓዘ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተሰያዩ። |
ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፥ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ ጌታ ገነት በግብጽ ምድር አምሳል ነበረ።
ሎጥ ከተለየው በኋላም ጌታ አብራምን አለው፦ “ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ፥
ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ፥ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፥ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።
ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኋላ እንዲህ አሉት፦ “ራስህን አድን፥ ወደ ኋላህ አትይ፥ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ።”
የምሥራቁ ድንበር በሐውራንና በደማስቆ፤ በገለዓድና በእስራኤልም ምድር መካከል እስከ ዮርዳኖስ ይሆናል። ከሰሜኑ ድንበር ጀምሮ እስከ ምሥራቁ ባሕር እስከ ታማር ድረስ፤ ይህም የምሥራቁ ድንበር ነው።
አንዳንዶችም ልምድ አድርገው እንደያዙት፥ መሰብሰባችንን አንተው፤ እርስ በርሳችን እንመካከር፤ ይልቁንም የቀኑን መቅረብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።