Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 13:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አብራም በከነዓን ምድር ተቀመጠ ሎጥም በአገሩ ሜዳ ባሉት ከተሞች ተቀመጠ፥ እስከ ሰዶምም ድረስ ድንኳኑን አዘዋወረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አብራም መኖሪያውን በከነዓን ምድር አደረገ፤ ሎጥ ግን በረባዳው ሜዳ ውስጥ ባሉት ከተሞች መካከል በሰዶም አቅራቢያ ድንኳኑን ተከለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አብራም በከነዓን ኖረ፤ ሎጥ ግን በሸለቆው ውስጥ ባሉት ከተሞች መካከል ተቀመጠ፤ በሰዶምም አጠገብ ድንኳኑን ተከለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አብ​ራም በከ​ነ​ዓን ምድር ተቀ​መጠ፤ ሎጥም በጎ​ረ​ቤት ሕዝ​ቦች ከተማ ተቀ​መጠ፤ ድን​ኳ​ኑ​ንም በሰ​ዶም ተከለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አብራም በከነዓን ምድር ተቀመጠ ሎጥም በአገሩ ሜድ ባሉት ከተሞች ተቀመጠ፥ እስከ ስዶም ሰዎች ድረስ ድንኳኑን አዘዋወረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 13:12
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፥ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚያ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው።


ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፥ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ። ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ አላቸውም፦


በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብራምን የወንድም ልጅ ሎጥን ደግሞ ከብቱንም ወስደው ሄዱ።


አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”


የክፉ አድራጊዎቸን ማኅበር ጠላሁ፥ ከክፉዎችም ጋር አልቀመጥም።


እነዚያንም ከተሞች፥ በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ፥ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ፥ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ።


ሎጥም በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን አገር ሁሉ መረጠ፥ ሎጥም ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፥ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተለያዩ።


ከሰዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገሞራ ንጉሥ ከብርሳ፥ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፥ ከሰቦይም ንጉሥ ከሰሜበር፥ ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥም ጋር ሰልፍ አደረጉ።


እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች