Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 19:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኋላ እንዲህ አሉት፦ “ራስህን አድን፥ ወደ ኋላህ አትይ፥ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እንዳወጧቸውም፣ መልአኩ፣ “ሕይወታችሁን ለማትረፍ ፈጥናችሁ ሽሹ፤ መለስ ብላችሁ ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ከረባዳው ስፍራ እንኳ ቆም አትበሉ፤ ወደ ተራራው ሽሹ፤ አለዚያ ትጠፋላችሁ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ካወጡአቸውም በኋላ ከመላእክቱ አንዱ “ሕይወታችሁን አድኑ! ወደ ኋላ አትመልከቱ! በሸለቆው ውስጥ አትዘግዩ፤ እንዳትሞቱ ወደ ተራራው ሽሹ!” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እን​ዲህ አሉት፥ “ራስ​ህን አድን፤ ወደ ኋላም አት​መ​ል​ከት፤ አን​ተ​ንም መከራ እን​ዳ​ታ​ገ​ኝህ በዚች ሀገር በዳ​ር​ቻ​ዋና በተ​ራ​ራዋ አት​ቁም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኍላ እንዲህ አለው ራስህን አድን ወደ ኍላህ አትይ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 19:17
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስ ግን፦ “የሞፈሩን ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ማንም ሰው ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም፤” አለው።


የሎጥም ሚስት ወደ ኋላዋ ተመለከተች፥ የጨው ሐውልትም ሆነች።


በቶሎ ወደዚያ ሸሽትህ አምልጥ፥ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ጾዓር ተባለ።


ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ እርሱ ጥምቀት ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቁጣ እንድታመልጡ ማን አመለከታችሁ?


ሸሽታችሁ ራሳችሁን አድኑ፤ በምድረ በዳ እንዳለ ቁጥቋጦ ሁኑ።


ኤልያስም ስለ ፈራ ሕይወቱን ለማትረፍ ከአገልጋዩ ጋር በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ ከተማ ሄደ። አገልጋዩንም በዚያ ተወው።


ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፥ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ ጌታ ገነት በግብጽ ምድር አምሳል ነበረ።


የዕርገት መዝሙር። ዐይኖቼን ወደ ተራሮቹ አነሣሁ፥ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ?


ሳኦልም የዳዊትን ቤት ከበው በማለዳ እንዲገድሉት ሰዎችን ላከ። የዳዊት ሚስት ሜልኮል ግን፥ “ሕይወትህን ለማትረፍ በዚህች ሌሊት ካልሸሸህ፥ በነገው ቀን ትገደላለህ” ብላ አስጠነቀቀችው።


ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ፥ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር።


እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ ይህንኑ አረጋግጠውልናል።


በሲዲም ሸለቆ ግን የዝፍት ጉድጓዶች ነበሩበት። የሰዶም ንጉሥ የገሞራ ንጉሥም ሸሹና ወደዚያ ወደቁ፥ የቀሩትም ወደ ተራራ። ሸሹ።


ሎጥም፥ አላቸው፦ “ጌቶቼ ሆይ፥ እንዲህስ አይሁን፥


ሎጥም ከዞዓር ወጣ፥ በዞዓር ይቀመጥ ዘንድ ስለ ፈራም ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራ ተቀመጠ፥ በዋሻም ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር ተቀመጠ።


እርሱም ለማኅበሩ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “እባካችሁ፥ ከእነዚህ ክፉዎች ድንኳን ርቃችሁ ገለል በሉ፤ በኃጢአታቸውም ሁሉ እንዳትጠፉ የእነርሱ የሆነውን ሁሉ አትንኩ።”


አሁንም ነዪ፥ የልጅሽን የሰሎሞንን ነፍስና የአንቺን ነፍስ እንድታድኝ እመክርሻለሁ።


ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች