Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 10:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 አንዳንዶችም ልምድ አድርገው እንደያዙት፥ መሰብሰባችንን አንተው፤ እርስ በርሳችን እንመካከር፤ ይልቁንም የቀኑን መቅረብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 አንዳንዶች ማድረጉን እንደተዉት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም ቀኑ እየተቃረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችን እንበረታታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ዘወትር እየተገናኘን እርስ በርሳችን እንበረታታ እንጂ አንዳንዶች ማድረግ እንደ ለመዱት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም የጌታ መምጫ ቀን መቃረቡን እያስታወሳችሁ ይህን ነገር በይበልጥ አድርጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሌሎች ልማድ አድ​ር​ገው እንደ ያዙት ማኅ​በ​ራ​ች​ንን አን​ተው፤ እርስ በር​ሳ​ችን እን​መ​ካ​ከር እንጂ፤ ይል​ቁ​ንም ቀኑ ሲቀ​ርብ እያ​ያ​ችሁ አብ​ል​ጣ​ችሁ ይህን አድ​ርጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 10:25
32 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እውነት እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ አገር ይቀልላቸዋል።


ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው አለሁና።”


የማይቀበለኝ ቃሌንም የማይሰማ እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።


ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቆለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን።


በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥


በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቁረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።


ከሳምንቱም በመጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰብስበን ሳለን፥ ጳውሎስ በነገው ሊሄድ ስላሰበ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር፤ እስከ መንፈቀ ሌሊትም ነገሩን አስረዘመ።


ምክር ከሆነ መምከር፤ መስጠት ከሆነ በልግስና መስጠት፤ ማስተዳደር ከሆነ በትጋት ማስተዳደር፤ ምሕረት ማድረግ ከሆነ በደስታ መማር።


በአንድነት በምትሰበሰቡበት ጊዜ የምትበሉት የጌታ እራት አይደለም።


እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ምእመናን በአንድነት በተሰበሰቡበት፥ ሁሉም በልሳን በመናገር ላይ እያሉ፥ እንግዶች ወይም የማያምኑ ሰዎች ወደ ጉባኤው ቢገቡ፥ አብደዋል አይሉምን?


ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽ፥ ለማበረታታትና ለማጽናናት ለሰው ይናገራል።


የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ፥ ያ ቀን በገሃድ ያሳያልና፤ የእያንዳንዱም ሥራ ምን መሆኑን እሳቱ ራሱ ይፈትነዋል።


ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር፥ በጌታችን ኢየሱስ ስም ተሰብስባችሁ፥ መንፈሴም አብሮችሁ ነው፥


ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ። ጌታ መምጫው ቀርቦአል።


ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በእነዚህ ቃላት ተጽናኑ።


ስለዚህ እናንተ በእርግጥ እያደረጋችሁት እንዳላችሁት፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ አንዱም ሌላውን ያንጸው።


ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተሳሰብ፤


ምክንያቱም ገና “በጣም ጥቂት ጊዜ፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል፥ አይዘገይምም፤


ወንድሞች ሆይ! ይህን በጥቂት ቃል የጻፍኩላችሁን የምክርን ቃል እንድትታገሡ እመክራችኋለሁ።


ነገር ግን ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ፥ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ፥ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ።


እናንተም እንዲሁ ታገሡ፤ ልባችሁንም አጽኑ፤ ምክንያቱም የጌታ መምጫ ተቃርቦአልና።


የሁሉ ነገር መጨረሻ ተቃርቧል፤ እንግዲህ መጸለይ እንድትችሉ የረጋ አእምሮ ይኑራችሁ፤ በመጠንም ኑሩ።


እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚጠፉ ከሆነ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል መኖር አይገባችሁም?


ስለዚህ ወዳጆች ሆይ! ይህን ሁሉ እየተጠባበቃችሁ፥ ጌታ ያለ ነውር ወይም ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም እንዲያገኛችሁ በትጋት ኑሩ፤


አንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው፥ ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃና ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።


እነዚህ መለያየትን የሚፈጥሩ ፍጥረታውያን የሆኑ፥ መንፈስም የሌላቸው ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች