Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ዕብራውያን 10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ስለ ኦሪት

1 ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እው​ነ​ተኛ አም​ሳል ሳይ​ሆን የነ​ገር ጥላ አለ​ውና፤ ስለ​ዚ​ህም በየ​ዓ​መቱ ዘወ​ትር በሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት በዚያ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቀ​ር​ቡ​ትን ሊፈ​ጽም ከቶ አይ​ች​ልም።

2 ይህስ ባይ​ሆን ከሚ​ሠ​ዉት መሥ​ዋ​ዕት ባረፉ ነበር፥ ለሚ​ሠ​ዉት ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ቸው ነበ​ርና፥ ባአ​ንድ ጊዜም ያነ​ጻ​ቸው ነበ​ርና።

3 ነገር ግን በዚ​ያው መሥ​ዋ​ዕት በየ​ዓ​መቱ የኀ​ጢ​አት መታ​ሰ​ቢያ አድ​ር​ገው የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ነበ​ራ​ቸው።

4 የላ​ምና የፍ​የል ደም ኀጢ​አ​ትን ሊያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ አይ​ች​ል​ምና።

5 ስለ​ዚ​ህም ወደ ዓለም በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ እን​ዲህ አለ፥ “መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አል​ወ​ደ​ድ​ህም፤ ሥጋን አለ​በ​ስ​ኸኝ እንጂ።

6 በሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስለ ኀጢ​አት በሚ​ቀ​ር​በው መሥ​ዋ​ዕት ደስ አላ​ለ​ህም።

7 ያን​ጊዜ እነሆ፥ በመ​ጽ​ሐፍ ራስ ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ፈቃ​ድ​ህን አደ​ርግ ዘንድ መጥ​ቻ​ለሁ አልሁ።”

8 በዚህ ላይ “መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና መባን፥ በሙሉ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም፥ ስለ ኀጢ​አ​ትም የሚ​ሠዋ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አል​ወ​ደ​ድ​ህም፤ በእ​ር​ሱም ደስ አላ​ለ​ህም” ብሎ ተና​ገረ፤ እነ​ዚ​ህም እንደ ሕግ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።

9 ከዚህ በኋላ፥ “አም​ላኬ ሆይ፥ ፈቃ​ድ​ህን አደ​ርግ ዘንድ እነሆ፥ መጣሁ” አለ፤ ይህ ቃል የኋ​ለ​ኛ​ውን ያቆም ዘንድ የፊ​ተ​ኛ​ውን ያፈ​ር​ሳል።

10 በፈ​ቃ​ዱም አንድ ጊዜ በተ​ደ​ረ​ገው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሥ​ጋዉ ቍር​ባን ተቀ​ደ​ስን።

11 ሊቀ ካህ​ና​ትም ሁሉ ዘወ​ትር እያ​ገ​ለ​ገለ ይቆም ነበር፤ ፈጽሞ ኀጢ​አት ማስ​ተ​ስ​ረይ የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ብቻም ይሠዋ ነበር።

12 እርሱ ግን ስለ ኀጢ​አት አን​ድን መሥ​ዋ​ዕት ለዘ​ለ​ዓ​ለም አቅ​ርቦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ተቀ​መጠ።

13 እን​ግ​ዲህ ጠላ​ቶቹ ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ወ​ድቁ ድረስ ይጠ​ብ​ቃል።

14 ለሚ​ቀ​ደ​ሱ​ትም ለዘ​ለ​ዓ​ለም የም​ት​ሆን አን​ዲት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ።

15 መን​ፈስ ቅዱ​ስም ምስ​ክ​ራ​ችን ነው።

16 “ከእ​ነ​ዚያ ወራ​ቶች በኋላ የም​ገ​ባ​ላ​ቸው ኪዳን ይህቺ ናት ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ሕጌን በል​ባ​ቸው አኖ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በል​ቡ​ና​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ ካለ በኋላ።

17 ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና በደ​ላ​ቸ​ውን ደግሜ አላ​ስ​ብ​ባ​ቸ​ውም” ብሏል።

18 እን​ዲ​ህም ኀጢ​አት የሚ​ሰ​ረይ ከሆነ፥ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አያ​ስ​ፈ​ል​ግም።


ስለ ወን​ጌል ካህ​ናት

19 እን​ግ​ዲህ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ደም ወደ መቅ​ደስ ለመ​ግ​ባት ባለ​ሙ​አ​ል​ነት አለን።

20 በሥ​ጋው መጋ​ረጃ በኩል የሕ​ይ​ወ​ት​ንና የጽ​ድ​ቅን መን​ገድ ፈጽሞ አድ​ሶ​ል​ና​ልና።

21 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ታላቅ ካህን አለን።

22 እን​ግ​ዲህ ከክፉ ሕሊና ለመ​ን​ጻት ልባ​ች​ንን ተረ​ጭ​ተን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም በጥሩ ውኃ ታጥ​በን በተ​ረ​ዳ​ን​በት እም​ነት በቅን ልብ እን​ቅ​ረብ።

23 እን​ግ​ዲህ የማ​ይ​ና​ወ​ጠ​ውን የተ​ስ​ፋ​ች​ንን እም​ነት እና​ጽና፤ ተስፋ የሰጠ እርሱ የታ​መነ ነውና።

24 በፍ​ቅ​ርና በበጎ ምግ​ባ​ርም ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችን ጋር እን​ፎ​ካ​ከር።

25 ሌሎች ልማድ አድ​ር​ገው እንደ ያዙት ማኅ​በ​ራ​ች​ንን አን​ተው፤ እርስ በር​ሳ​ችን እን​መ​ካ​ከር እንጂ፤ ይል​ቁ​ንም ቀኑ ሲቀ​ርብ እያ​ያ​ችሁ አብ​ል​ጣ​ችሁ ይህን አድ​ርጉ።

26 እው​ነ​ትን ካወ​ቅ​ናት በኋላ፥ ተጋ​ፍ​ተን ብን​በ​ድል ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አይ​ኖ​ርም።

27 ነገር ግን የሚ​ያ​ስ​ፈራ ፍርድ ከሓ​ዲ​ዎ​ች​ንም የሚ​በ​ላ​ቸው የቅ​ናት እሳት ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል።

28 ከሙሴ ሕግ የተ​ላ​ለፈ ቢኖር ሁለት፥ ወይም ሦስት ምስ​ክ​ሮች ከመ​ሰ​ከ​ሩ​በት ያለ ምሕ​ረት ይሞ​ታል።

29 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ የከዳ፥ ያን​ንም የተ​ቀ​ደ​ሰ​በ​ትን የኪ​ዳ​ኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቈ​ጠረ፥ የጸ​ጋ​ው​ንም መን​ፈስ ያክ​ፋፋ እን​ዴት ይልቅ የሚ​ብስ ቅጣት የሚ​ገ​ባው ይመ​ስ​ላ​ች​ኋል?

30 “እኔ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ እኔም ብድ​ራ​ትን እመ​ል​ሳ​ለሁ፥” ያለ​ውን እና​ው​ቀ​ዋ​ለ​ንና፤ ዳግ​መ​ኛም “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ይፈ​ር​ዳል።”

31 በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ እጅግ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ነው።

32 እና​ንተ የተ​ጠ​መ​ቃ​ች​ሁ​በ​ት​ንና ብዙ መከራ የታ​ገ​ሣ​ች​ሁ​በ​ትን የቀ​ደ​መ​ውን ዘመን አስቡ፤

33 እና​ንተ ተሰ​ድ​ባ​ችሁ ነበር፤ መከ​ራም አጽ​ን​ተ​ው​ባ​ችሁ ነበር፤ ተዘ​ባ​ብ​ተ​ው​ባ​ች​ሁም ነበር፤ በዚ​ህም መን​ገድ እን​ዲህ ከሆ​ኑት ጋር ተባ​ብ​ራ​ችሁ ነበር።

34 በእ​ስ​ራ​ቴም ጊዜ ከእኔ ጋር በመ​ከራ ተባ​ብ​ራ​ች​ኋል፤ የገ​ን​ዘ​ባ​ች​ሁ​ንም መዘ​ረፍ በደ​ስታ ተቀ​ብ​ላ​ች​ኋል፤ በሰ​ማ​ያት ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ከዚህ የሚ​በ​ል​ጥና የተ​ሻለ ገን​ዘብ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።

35 ትል​ቁን ዋጋ​ች​ሁን የም​ታ​ገ​ኙ​ባ​ትን መታ​መ​ና​ች​ሁን አት​ጣሉ።

36 ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ አድ​ር​ጋ​ችሁ የተ​ሰ​ጣ​ች​ሁን ተስፋ ታገኙ ዘንድ መታ​ገሥ ያስ​ፈ​ል​ጋ​ች​ኋል።

37 “ገና ጥቂት ቀን አለና፤ የሚ​መ​ጣ​ውም ፈጥኖ ይደ​ር​ሳል፥ አይ​ዘ​ገ​ይ​ምም።

38 ጻድቅ በእ​ም​ነት ይድ​ናል፤ ወደ​ኋላ ቢመ​ለስ ግን ልቡ​ናዬ በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ትም።”

39 እኛ ግን ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ሊያ​ድኑ ከሚ​ያ​ም​ኑት ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚ​ያ​ፈ​ገ​ፍ​ጉት አይ​ደ​ለ​ንም።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች