Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የላ​ምና የፍ​የል ደም ኀጢ​አ​ትን ሊያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ አይ​ች​ል​ምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ምክንያቱም የኰርማዎችና የፍየሎች ደም ኀጢአትን ማስወገድ አይችልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን ለማስወገድ አይችልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የወይፈኖችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን ማስወገድ አይችልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 10:4
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሬን የሚ​ሠ​ዋ​ልኝ ኃጥእ ውሻን እን​ደ​ሚ​ያ​ር​ድ​ልኝ ነው፤ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን የሚ​ያ​ቀ​ር​ብም የእ​ሪ​ያን ደም እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ ነው፤ ዕጣ​ን​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ያ​ጥን አም​ላ​ክን እን​ደ​ሚ​ፀ​ርፍ ነው፤ እነ​ዚህ የገዛ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን መረጡ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ይላ​ታል።


ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣ​ንን፥ ከሩ​ቅም ሀገር ቀረ​ፋን ታቀ​ር​ቡ​ል​ኛ​ላ​ችሁ? የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን አል​ቀ​በ​ለ​ውም፤ ቍር​ባ​ና​ች​ሁም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ኝም።


እስ​ራ​ኤል ሆይ! በኀ​ጢ​አ​ትህ ወድ​ቀ​ሃ​ልና ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለስ።


ከመ​ሥ​ዋ​ዕት ይልቅ ምሕ​ረ​ትን፥ ከሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማወቅ እወ​ድ​ዳ​ለ​ሁና።


በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኀይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው፡” አለው።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ዮሐ​ንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን አይቶ እን​ዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ።


ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ባራ​ቅ​ሁ​ላ​ቸው ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር የም​ገ​ባው ኪዳን ይህ ነው።”


ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እው​ነ​ተኛ አም​ሳል ሳይ​ሆን የነ​ገር ጥላ አለ​ውና፤ ስለ​ዚ​ህም በየ​ዓ​መቱ ዘወ​ትር በሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት በዚያ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቀ​ር​ቡ​ትን ሊፈ​ጽም ከቶ አይ​ች​ልም።


ሊቀ ካህ​ና​ትም ሁሉ ዘወ​ትር እያ​ገ​ለ​ገለ ይቆም ነበር፤ ፈጽሞ ኀጢ​አት ማስ​ተ​ስ​ረይ የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ብቻም ይሠዋ ነበር።


በዚህ ላይ “መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና መባን፥ በሙሉ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም፥ ስለ ኀጢ​አ​ትም የሚ​ሠዋ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አል​ወ​ደ​ድ​ህም፤ በእ​ር​ሱም ደስ አላ​ለ​ህም” ብሎ ተና​ገረ፤ እነ​ዚ​ህም እንደ ሕግ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።


ነገር ግን ለሚ​ያ​ቀ​ር​በው ሰው ግዳጅ መፈ​ጸም የማ​ይ​ቻ​ለ​ውን መባና መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት የነ​በ​ረው ለዚህ ዘመን ምሳሌ ሆነ።


እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች