Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 25:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 ከገ​ዛ​ውም ሰው ጋር ከገ​ዛ​በት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ ይቍ​ጠር፤ የሽ​ያ​ጩም ብር እንደ ዓመ​ታቱ ቍጥር ይሁን፤ እንደ ምን​ደ​ኛ​ውም ዘመን ከእ​ርሱ ጋር ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 እርሱም ራሱን ከሸጠበት ዓመት አንሥቶ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ያለውን ጊዜ ከገዛው ሰው ጋራ በመሆን ይቍጠር፤ ነጻ የሚለቀቅበትም ዋጋ በእነዚያ ዓመታት ለአንድ ቅጥር ሠራተኛ በሚከፈለው መሠረት ይተመናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 ከገዛውም ሰው ጋር ለገዢው ራሱን ከሸጠበት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ያለውን ጊዜ ያሰላል፤ የሽያጩም ብር እንደ ዓመታቱ ቍጥር ይሆናል፤ ከባለቤቱም ጋር የነበረበት ጊዜ ተቀጣሪ አገልጋይ እንደ ነበረበት ጊዜ ተደርጎ ይተመናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 ይህም በሚሆንበት ጊዜ ከገዛው ሰው ጋር ይመካከር፤ ዘመኑንም እርሱ ራሱን ከሸጠበት ዓመት ጀምሮ እስከ ተከታዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቊጠሩት፤ ስለ እርሱም ነጻ መለቀቅ ተገቢውን ዋጋ በእነዚያ ዓመቶች ውስጥ ተቀጥሮ በሚሠራ ሰው ልክ ይተምኑት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 ከገዛውም ሰው ጋር ከገዛበት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቍጠር፤ የሽያጩም ብር እንደ ዓመታቱ ቍጥር ይሁን፤ እንደ ምንደኛውም ዘመን ከእርሱ ጋር ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 25:50
10 Referencias Cruzadas  

“እንደ ምን​ደኛ ሕይ​ወ​ቱን እን​ዲ​ጠ​ባ​በ​ቃት፥ ያርፍ ዘንድ ከእ​ርሱ ዘወር በል።


አሁ​ንም እን​ዲህ እላ​ለሁ፤ በሦ​ስት ዓመት ውስጥ እንደ ምን​ደኛ ዓመት የሞ​ዓብ ክብር ከብዙ ሀብ​ትዋ ጋር ይዋ​ረ​ዳል፤ በቍ​ጥ​ርም ጥቂት ይቀ​ራል፤ ክብ​ር​ዋም አይ​ገ​ኝም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እን​ዲህ ብሎ​ኛ​ልና፥ “እንደ ምን​ደኛ ዓመት በአ​ንድ ዓመት ውስጥ የቄ​ዳር ልጆች ክብር ሁሉ ይጠ​ፋል፤


ለራ​ሱም ዕዳ​ውን መክ​ፈል ባይ​ችል፥ ሽያጩ በገ​ዛው ሰው እጅ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ ይቀ​መጥ፤ በኢ​ዮ​ቤ​ል​ዩም ዓመት ይውጣ፤ እር​ሱም ወደ ርስቱ ይመ​ለስ።


እንደ ምን​ደ​ኛና እንደ ስደ​ተኛ ከአ​ንተ ጋር ይሁን፤ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመ​ትም ያገ​ል​ግ​ልህ።


ወይም አጎቱ ወይም የአ​ጎቱ ልጅ ይቤ​ዠው፤ ወይም ከወ​ገኑ ለእ​ርሱ የቀ​ረበ ዘመድ ይቤ​ዠው፤ ወይም እርሱ እጁ ቢረ​ጥብ ራሱን ይቤ​ዠው።


ብዙ ዓመ​ታ​ትም ቢቀሩ እንደ እነ​ርሱ ቍጥር ከሽ​ያጩ ብር የመ​ቤ​ዠ​ቱን ዋጋ ይመ​ልስ።


በየ​ዓ​መቱ እንደ ምን​ደኛ ከእ​ርሱ ጋር ይኑር፤ በፊ​ትህ እንደ ቀደ​መው አያ​ስ​ጨ​ን​ቀው።


እር​ሱ​ንም አር​ነት ባወ​ጣ​ኸው ጊዜ የም​ን​ደ​ኝ​ነ​ቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድ​ርጎ ስድ​ስት ዓመት አገ​ል​ግ​ሎ​ሃ​ልና አያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ት​ሠ​ራው ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos