ዘሌዋውያን 25:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)50 ከገዛውም ሰው ጋር ለገዢው ራሱን ከሸጠበት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ያለውን ጊዜ ያሰላል፤ የሽያጩም ብር እንደ ዓመታቱ ቍጥር ይሆናል፤ ከባለቤቱም ጋር የነበረበት ጊዜ ተቀጣሪ አገልጋይ እንደ ነበረበት ጊዜ ተደርጎ ይተመናል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም50 እርሱም ራሱን ከሸጠበት ዓመት አንሥቶ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ያለውን ጊዜ ከገዛው ሰው ጋራ በመሆን ይቍጠር፤ ነጻ የሚለቀቅበትም ዋጋ በእነዚያ ዓመታት ለአንድ ቅጥር ሠራተኛ በሚከፈለው መሠረት ይተመናል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም50 ይህም በሚሆንበት ጊዜ ከገዛው ሰው ጋር ይመካከር፤ ዘመኑንም እርሱ ራሱን ከሸጠበት ዓመት ጀምሮ እስከ ተከታዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቊጠሩት፤ ስለ እርሱም ነጻ መለቀቅ ተገቢውን ዋጋ በእነዚያ ዓመቶች ውስጥ ተቀጥሮ በሚሠራ ሰው ልክ ይተምኑት። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)50 ከገዛውም ሰው ጋር ከገዛበት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቍጠር፤ የሽያጩም ብር እንደ ዓመታቱ ቍጥር ይሁን፤ እንደ ምንደኛውም ዘመን ከእርሱ ጋር ይሁን። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)50 ከገዛውም ሰው ጋር ከገዛበት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቍጠር፤ የሽያጩም ብር እንደ ዓመታቱ ቍጥር ይሁን፤ እንደ ምንደኛውም ዘመን ከእርሱ ጋር ይሁን። Ver Capítulo |