Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 15:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሶም​ሶ​ንም ሄዶ ሦስት መቶ ቀበ​ሮ​ችን ያዘ፤ ችቦም ወስዶ ሁለት ሁለ​ቱን ቀበ​ሮ​ዎች በጅ​ራ​ታ​ቸው አሰረ፤ በሁ​ለ​ቱም ጅራ​ቶች መካ​ከል አንድ ችቦ አደ​ረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም ወጥቶ በመሄድ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፤ የሁለት ሁለቱን ጭራ አንድ ላይ ካሰረ በኋላ ችቦ ወስዶ ጥንድ ሆኖ ከተያያዘው ጭራ ጋራ አሰረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከዚያም ወጥቶ በመሄድ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፤ የሁለት ሁለቱን ጭራ አንድ ላይ ካሰረ በኋላ ችቦ ወስዶ ጥንድ ሆኖ ከተያያዘው ጭራ ጋር አሰረው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሄዶም ሦስት መቶ ቀበሮዎችን በማደን ያዘ፤ ጥንድ ጥንድ አድርጎ ጭራቸውን በማያያዝ በገመድ አሰረ፤ ችቦዎችም አምጥቶ በጭራቸው መካከል አሰረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሶምሶንም ሄዶ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፥ ችቦም ወስዶ ሁለት ሁለቱንም ቀበሮዎች በጅራታቸው አሰረ፥ በሁለቱም ጅራቶች መካከል አንድ ችቦ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 15:4
8 Referencias Cruzadas  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “በእ​ር​ሻዬ አጠ​ገብ ያለ​ች​ውን የኢ​ዮ​አ​ብን እርሻ እዩ፤ በዚ​ያም ገብስ አለው፤ ሄዳ​ችሁ በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉት” አላ​ቸው። የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም ብላ​ቴ​ኖች እር​ሻ​ውን አቃ​ጠ​ሉት። የኢ​ዮ​አ​ብም አሽ​ከ​ሮች ልብ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ተመ​ል​ሰው፥ “የአ​ቤ​ሴ​ሎም አሽ​ከ​ሮች እር​ሻ​ህን በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉት” ብለው ነገ​ሩት።


ጻድቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ዋል፥ በእ​ር​ሱም ይታ​መ​ናል፤ ልባ​ቸ​ውም የቀና ሁሉ ይከ​ብ​ራሉ።


የወ​ይን ቦታ​ችን ያብብ ዘንድ፥ የወ​ይ​ና​ች​ንን ቦታ የሚ​ያ​ጠ​ፉ​ትን ጥቃ​ቅ​ኑን ቀበ​ሮች አጥ​ም​ዳ​ችሁ ያዙ​ልን።


እን​ዲ​ህም በለው፥ “ተጠ​በቅ፥ ዝምም በል፤ አት​ፍራ፤ ከእ​ነ​ዚህ ከሚ​ጤሱ ሁለት የእ​ን​ጨት ጠለ​ሸ​ቶች፥ የተ​ነሣ ልብህ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ ከተ​ቈ​ጣሁ በኋላ ይቅር እላ​ለ​ሁና።


የጽ​ዮን ተራራ ባድማ ሆና​ለ​ችና፥ ቀበ​ሮ​ዎ​ችም ተመ​ላ​ል​ሰ​ው​ባ​ታ​ልና።


ሶም​ሶ​ንም፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ክፉ ባደ​ርግ እኔ ንጹሕ ነኝ” አላ​ቸው።


ችቦ​ው​ንም አን​ድዶ በቆ​መው በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እህል መካ​ከል ሰደ​ዳ​ቸው፤ ነዶ​ው​ንም፥ ክም​ሩ​ንም፥ የቆ​መ​ዉ​ንም እህል፥ ወይ​ኑ​ንም፥ ወይ​ራ​ዉ​ንም አቃ​ጠለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos