Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 15:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሄዶም ሦስት መቶ ቀበሮዎችን በማደን ያዘ፤ ጥንድ ጥንድ አድርጎ ጭራቸውን በማያያዝ በገመድ አሰረ፤ ችቦዎችም አምጥቶ በጭራቸው መካከል አሰረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም ወጥቶ በመሄድ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፤ የሁለት ሁለቱን ጭራ አንድ ላይ ካሰረ በኋላ ችቦ ወስዶ ጥንድ ሆኖ ከተያያዘው ጭራ ጋራ አሰረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከዚያም ወጥቶ በመሄድ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፤ የሁለት ሁለቱን ጭራ አንድ ላይ ካሰረ በኋላ ችቦ ወስዶ ጥንድ ሆኖ ከተያያዘው ጭራ ጋር አሰረው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሶም​ሶ​ንም ሄዶ ሦስት መቶ ቀበ​ሮ​ችን ያዘ፤ ችቦም ወስዶ ሁለት ሁለ​ቱን ቀበ​ሮ​ዎች በጅ​ራ​ታ​ቸው አሰረ፤ በሁ​ለ​ቱም ጅራ​ቶች መካ​ከል አንድ ችቦ አደ​ረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሶምሶንም ሄዶ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፥ ችቦም ወስዶ ሁለት ሁለቱንም ቀበሮዎች በጅራታቸው አሰረ፥ በሁለቱም ጅራቶች መካከል አንድ ችቦ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 15:4
8 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም አቤሴሎም አገልጋዮቹን “ተመልከቱ፤ የኢዮአብ እርሻ ከእኔ እርሻ ቀጥሎ ሲሆን የገብስ ሰብል ይገኝበታል፤ ስለዚህም ሂዱና በእሳት አቃጥሉት” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ሄደው ሰብሉን በእሳት አቃጠሉ።


በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሬሳቸውንም ቀበሮዎች ይበሉታል።


ሰውን አታሎ “በቀልድ ነው ያደረግኹት” የሚል ሰው በአደገኛ የጦር መሣሪያ እንደሚጫወት ዕብድ ሰው ነው።


ወይናችን አብቦአል፤ ስለዚህ የወይን ተክላችንን እንዳያጠፉብን ቀበሮዎችን፥ እነኛን ትናንሽ ቀበሮዎችን አጥምዳችሁ ያዙልን።


ረጋ እንዲል፤ እንዳይፈራ፥ በእሳት ተቀጣጥሎ እንደሚነድ እንደ ግንድ ጢስ በሆኑት በሬዚንና በሶርያው በሬማልያ ልጅ ምክንያት እንዳይሸበር ንገረው።


የጽዮን ተራራ ባድማ ስለ ሆነች፥ ቀበሮዎች ይመላለሱበታል።


ሶምሶንም “ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ክፉ ነገር ባደርግ አልወቀስበትም!” አለ።


ከዚያም በኋላ በችቦዎቹ ላይ እሳት በማቀጣጠል ቀበሮዎቹን ገና ወዳልታጨደው ወደ ፍልስጥኤማውያን የስንዴ ሰብል ውስጥ ለቀቃቸው፤ በዚህም ዐይነት ታጭዶ የተከመረውን ብቻ ሳይሆን ገና በማሳ ላይ ያለውን ስንዴ፥ የወይራና የወይን ተክል ጭምር አቃጠለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos