Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 11:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሴቶች ልጆች ለገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊዉ ለዮ​ፍ​ታሔ ልጅ በዓ​መት አራት ቀን ያለ​ቅ​ሱ​ላት ዘንድ በዓ​መት በዓ​መት ይሄዱ ነበር። ይህ​ችም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ሥር​ዐት ሆነች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 የእስራኤል ወጣት ሴቶች የገለዓዳዊውን የዮፍታሔን ልጅ በማሰብ በየዓመቱ እየወጡ የአራት ቀን ሐዘን ያደርጉላታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 የእስራኤል ወጣት ሴቶች የገለዓዳዊውን የዮፍታሔን ልጅ በማሰብ በየዓመቱ እየወጡ የአራት ቀን ኀዘን ያደርጉላታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 የእስራኤላውያን ወጣት ሴቶች ልጆች በየዓመቱ ለአራት ቀን ያኽል ከቤታቸው ርቀው እየሄዱ ለገለዓዳዊው ለዮፍታሔ ሴት ልጅ ማዘናቸውና ማልቀሳቸው የተለመደ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 የእስራኤልም ሴቶች ልጆች በዓመት በዓመቱ እየሄዱ የገለዓዳዊውን የዮፍታሔን ልጅ በዓመት አራት ቀን ሙሾ እንዲያወጡ በእስራኤል ዘንድ ልማድ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 11:40
6 Referencias Cruzadas  

ሰሎ​ሞ​ንም በየ​ዓ​መቱ ሦስት ጊዜ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና የሰ​ላ​ሙን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሠ​ራው መሠ​ዊያ ላይ ያሳ​ርግ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ባለው መሠ​ዊያ ላይ ዕጣን ያሳ​ርግ ነበር፤ ቤቱ​ንም ጨረሰ።


ኤር​ም​ያ​ስም ለን​ጉሡ ለኢ​ዮ​ስ​ያስ የል​ቅሶ ግጥም ገጠ​መ​ለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወን​ዶ​ችና ሴቶች መዘ​ም​ራን ሁሉ በል​ቅሶ ግጥ​ማ​ቸው ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ይና​ገሩ ነበር፤ ይህም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዘንድ ወግ ሆኖ በል​ቅሶ ግጥም ተጽ​ፎ​አል።


ሁለት ወርም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ወደ አባቷ ተመ​ለ​ሰች፤ ዮፍ​ታ​ሔም የተ​ሳ​ለ​ውን ስእ​ለት አደ​ረገ፤ እር​ስ​ዋም ወንድ አላ​ወ​ቀ​ችም ነበር።


የኤ​ፍ​ሬ​ምም ሰዎች ተሰ​በ​ሰቡ፤ ወደ ጻፎ​ንም ተሻ​ግ​ረው ዮፍ​ታ​ሔን፥ “ከአ​ሞን ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ስታ​ልፍ ከአ​ንተ ጋር እን​ድ​ን​ሄድ ስለ​ምን አል​ጠ​ራ​ኸ​ንም? ቤት​ህን በአ​ንተ ላይ በእ​ሳት እና​ቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለን” አሉት።


በብ​ዙ​ዎች ደስ​ተ​ኞች መካ​ከል መሰ​ን​ቆን ምቱ፤ በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ድቅ ሥራን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ውስጥ ጽድ​ቅ​ንና ኀይ​ልን ያቀ​ር​ባሉ። ያን​ጊ​ዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ወደ ከተ​ማ​ዎቹ ወረዱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos