Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 11:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ሁለት ወርም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ወደ አባቷ ተመ​ለ​ሰች፤ ዮፍ​ታ​ሔም የተ​ሳ​ለ​ውን ስእ​ለት አደ​ረገ፤ እር​ስ​ዋም ወንድ አላ​ወ​ቀ​ችም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ከሁለት ወር በኋላ ወደ አባቷ ተመለሰች፤ እርሱም የተሳለውን አደረገ፤ ድንግልም ነበረች። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ይህ በእስራኤል ልማድ ሆኖ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ከሁለት ወር በኋላ ወደ አባቷ ተመለሰች፤ እርሱም የተሳለውን አደረገ፤ ድንግልም ነበረች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህ በእስራኤል ልማድ ሆኖ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ከሁለት ወር በኋላ ወደ አባትዋ ቤት ተመልሳ መጣች፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ቃል የገባውን ስለት ፈጸመባት፤ እርስዋም ወንድ ያላወቀች ድንግል ነበረች። ከዚያም ጊዜ አንሥቶ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ሁለትም ወር ከተፈጸመ በኋላ ወደ አባትዋ ተመለሰች፥ እንደ ተሳለውም ስእለት አደረገባት፥ እርስዋም ወንድ አላወቀችም ነበር።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 11:39
12 Referencias Cruzadas  

ኤር​ም​ያ​ስም ለን​ጉሡ ለኢ​ዮ​ስ​ያስ የል​ቅሶ ግጥም ገጠ​መ​ለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወን​ዶ​ችና ሴቶች መዘ​ም​ራን ሁሉ በል​ቅሶ ግጥ​ማ​ቸው ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ይና​ገሩ ነበር፤ ይህም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዘንድ ወግ ሆኖ በል​ቅሶ ግጥም ተጽ​ፎ​አል።


በሬን የሚ​ሠ​ዋ​ልኝ ኃጥእ ውሻን እን​ደ​ሚ​ያ​ር​ድ​ልኝ ነው፤ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን የሚ​ያ​ቀ​ር​ብም የእ​ሪ​ያን ደም እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ ነው፤ ዕጣ​ን​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ያ​ጥን አም​ላ​ክን እን​ደ​ሚ​ፀ​ርፍ ነው፤ እነ​ዚህ የገዛ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን መረጡ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ይላ​ታል።


ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ አታ​ድ​ርግ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው በእ​ሳት ስለ​ሚ​ያ​ቃ​ጥሉ አሕ​ዛብ ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ርኩስ ነገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ላ​ልና።


ከአ​ሞን ልጆች ዘንድ በደ​ኅና በተ​መ​ለ​ስሁ ጊዜ፥ ከቤቴ ደጅ ወጥቶ የሚ​ቀ​በ​ለ​ኝን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ” ብሎ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ተሳለ።


እር​ሱም፥ “ሂጂ” አለ። ሁለት ወርም አሰ​ና​በ​ታት፤ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ች​ዋም ጋር ሄደች፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ ለድ​ን​ግ​ል​ናዋ አለ​ቀ​ሰች።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሴቶች ልጆች ለገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊዉ ለዮ​ፍ​ታሔ ልጅ በዓ​መት አራት ቀን ያለ​ቅ​ሱ​ላት ዘንድ በዓ​መት በዓ​መት ይሄዱ ነበር። ይህ​ችም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ሥር​ዐት ሆነች።


እር​ስ​ዋም፥ “አዶ​ናይ፥ የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! የባ​ር​ያ​ህን መዋ​ረድ ተመ​ል​ክ​ተህ ብታ​ስ​በኝ፥ ለባ​ር​ያ​ህም ወንድ ልጅ ብት​ሰጥ ዕድ​ሜ​ውን ሁሉ ለአ​ንተ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥም አይ​ጠ​ጣም። ምላ​ጭም በራሱ ላይ አይ​ደ​ር​ስም” ብላ ስእ​ለት ተሳ​ለች።


ሐና ግን ከእ​ርሱ ጋር አል​ወ​ጣ​ችም። ለባ​ል​ዋም፥ “ሕፃ​ኑን ጡት እስከ አስ​ጥ​ለው፥ ከእ​ኔም ጋር እስ​ኪ​ወ​ጣና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስ​ኪ​ታይ ድረስ አል​ወ​ጣም፤ በዚ​ያም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል” ብላ​ዋ​ለ​ችና።


እር​ስ​ዋም ከእ​ርሱ ጋር አንድ የሦ​ስት ዓመት ወይ​ፈን፥ እን​ጀራ፥ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁ​ማዳ የወ​ይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወጣች። በሴ​ሎም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገባች። ልጃ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ።


እኔም ደግሞ ዕድ​ሜ​ውን ሙሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።”


ሳሙ​ኤል ግን ገና ብላ​ቴና ሳለ የበ​ፍታ ኤፉድ ታጥቆ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያገ​ለ​ግል ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos