Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 32:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እና​ን​ተም፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብን አግ​ኝ​ተ​ናል፤ አብ​ዝ​ተ​ና​ልም እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ‘እኛ ጥበብ አግኝተናል፤ ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ይርታው’ አትበሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እናንተም፦ ጥበብን አግኝተናል፥ እግዚአብሔር ነው እንጂ ሰው አያሸንፈውም እንዳትሉ ተጠንቀቁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለኢዮብ ተገቢ መልስ ሊሰጠው የሚችል እግዚአብሔር እንጂ ሰው ስላልሆነ፥ እናንተ ጥበብን አግኝተናል ብላችሁ በከንቱ አትመኩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እናንተም፦ ጥበብን አግኝተናል፥ እግዚአብሔር ነው እንጂ ሰው አያሸንፈውም እንዳትሉ ተጠንቀቁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 32:13
23 Referencias Cruzadas  

አንተ፦ አብ​ራ​ምን ባለ​ጠጋ አደ​ረ​ግ​ሁት እን​ዳ​ትል፥ ከአ​ንተ ገን​ዘብ ሁሉ ፈት​ልም ቢሆን፥ የጫማ ማዘ​ቢ​ያም ቢሆን እን​ዳ​ል​ወ​ስድ፥


እን​ዲ​ህም አለ፥ “ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ራቁ​ቴን ወጥ​ቻ​ለሁ፥ ራቁ​ቴ​ንም ወደ ምድር እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጠ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነሣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ፈቀደ ሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ብ​ሔር ስም የተ​ባ​ረከ ይሁን።”


“በእ​ር​ግጥ እና​ንተ ዓይ​ነ​ተ​ኞች ሰዎች ናችሁ፤ ጥበ​ብም በእ​ና​ንተ ዘንድ ትፈ​ጸ​ማ​ለች።


እና​ንተ ወዳ​ጆቼ ሆይ፤ ማሩኝ፤ ማሩኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ዳስ​ሳ​ኛ​ለ​ችና።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ከኝ፥ መዓ​ቱ​ንም በእኔ ላይ እንደ አበዛ ዕወቁ።


እርሱ ግን፦ ወደ እር​ስዋ ተመ​ለ​ከ​ተና እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ከሰ​ነ​ፎች ሴቶች እንደ አን​ዲቱ ተና​ገ​ርሽ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መል​ካ​ሙን ተቀ​በ​ልን፥ ክፉ​ውን ነገ​ርስ አን​ታ​ገ​ሥ​ምን?” በዚህ በደ​ረ​ሰ​በት ሁሉ ኢዮብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በከ​ን​ፈሩ አል​በ​ደ​ለም።


በስ​ንዴ ፋንታ እን​ክ​ር​ዳድ፥ በገ​ብ​ስም ፋንታ ኵር​ን​ችት ይብ​ቀ​ል​ብኝ።” ኢዮ​ብም ነገ​ሩን ፈጸመ።


እን​ዲ​ሁም ልብ አደ​ረ​ግሁ፤ እነ​ሆም፥ ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ኢዮ​ብን የገ​ሠጸ፥ ወይም ለተ​ና​ገ​ረው ቃልን የመ​ለሰ የለም።


እና​ንተ ግን እን​ዲህ ያለ ነገር እን​ዲ​ና​ገር ለሰው መብት ሰጣ​ች​ሁት።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይጠ​ፋሉ፥ በቍ​ጣ​ውም መን​ፈስ ያል​ቃሉ።


እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍላጻ በሥ​ጋዬ ላይ ነው፤ መር​ዙም ደሜን ይመ​ጥ​ጣል። ለመ​ና​ገር ስጀ​ም​ርም ይወ​ጋ​ኛል።


ስለ​ዚህ፥ አንተ፥ “ጣዖቴ ይህን አድ​ር​ጎ​አል፤ የተ​ቀ​ረ​ጸው ምስ​ሌና ቀልጦ የተ​ሠ​ራው ምስ​ሌም ይህን አዘ​ዙኝ” እን​ዳ​ትል፥ የሚ​ሆ​ነ​ውን ከመ​ሆኑ በፊት ነገ​ር​ሁህ፤ አስ​ረ​ዳ​ሁ​ህም፤


እነ​ር​ሱም አሁን እንጂ ከጥ​ንት አል​ተ​ፈ​ጠ​ሩም፤ አን​ተም፥ “እነሆ፥ ዐው​ቄ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ” እን​ዳ​ትል ከዛሬ በፊት አል​ሰ​ማ​ሃ​ቸ​ውም።


ለክ​ፋት ጥበ​በ​ኞች ለሆኑ፥ እኛ ጠቢ​ባን ነን ለሚ​ሉም ወዮ​ላ​ቸው!


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀያ​ልም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ባለ​ጠ​ጋም በብ​ል​ጥ​ግ​ናው አይ​መካ፤


ከዳ​ን​ኤል ይልቅ አንተ ጥበ​በኛ ነህን? ብል​ሃ​ተ​ኞ​ችም በጥ​በ​ባ​ቸው አላ​ስ​ተ​ማ​ሩ​ህም።


እግዚአብሔርም የዳዊት ቤት ክብርና የኢየሩሳሌም ሰዎች ክብር በይሁዳ ክብር ላይ እንዳይታበይ የይሁዳን ድንኳኖች አስቀድሞ ያድናል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው።


ራሳ​ች​ሁን አታ​ስቱ፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ በዚህ ዓለም ጥበ​በኛ እንደ ሆነ የሚ​ያ​ስብ ሰው ጥበ​በኛ ይሆን ዘንድ ራሱን ዐላ​ዋቂ ያድ​ርግ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ከአ​ንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝ​ቶ​አል፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል፦ እጄ አዳ​ነኝ ብሎ እን​ዳ​ይ​ታ​በ​ይ​ብኝ እኔ ምድ​ያ​ምን በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos