Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 28:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም በብ​ል​ሃት ከተ​ጠ​ለፈ ከል​ብሰ መት​ክፉ ቋድ በላይ እን​ዲ​ሆን፥ ከል​ብሰ መት​ከ​ፉም እን​ዳ​ይ​ለይ፥ ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከቀ​ለ​በ​ቶቹ ወደ ልብሰ መት​ከፉ ቀለ​በ​ቶች በሰ​ማ​ያዊ ፈትል ያያ​ይ​ዙ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የደረት ኪሱም ቀለበቶች፣ የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ጋራ እንዳይላቀቅ፣ ከመታጠቂያው ጋራ በማገናኘት በሰማያዊ ገመድ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋራ ይያያዙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የደረት ኪሱም በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ በላይ እንዲሆን ከኤፉዱም እንዳይለይ፥ የደረት ኪሱን ከቀለበቶቹ ወደ ኤፉዱ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል ያያይዙታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በደረት ኪሱ ላይ ያሉትን ቀለበቶች በኤፉዱ ላይ ካሉት ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ድሪ እሰራቸው፤ በዚህ ዐይነት የደረት ኪሱ ከመታጠቂያው በላይ ስለሚሆን ልል አይሆንም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የደረቱም ኪስ በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቍድ በላይ እንዲሆን ከኤፉዱም እንዳይለይ፥ የደረቱን ኪስ ከቀለበቶቹ ወደ ኤፉዱ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል ያስሩታል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 28:28
9 Referencias Cruzadas  

መረ​ግ​ድም፥ ለል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓና ለደ​ረት ኪስ የሚ​ደ​ረግ ፈርጥ።


ደግ​ሞም ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች ሥራ፤ በል​ብሰ መት​ከፉ ፊት ከጫ​ን​ቃ​ዎች በታች በብ​ል​ሃት ከተ​ጠ​ለፈ ከል​ብሰ መት​ከፉ ቋድ በላይ በመ​ጋ​ጠ​ሚ​ያው አጠ​ገብ ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።


አሮ​ንም ወደ መቅ​ደስ በገባ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስሞች በፍ​ርዱ ልብሰ እን​ግ​ድዓ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸ​ከም።


“ቀሚ​ሱ​ንም ሁሉ ሰማ​ያዊ አድ​ር​ገው።


በሰ​ማ​ያ​ዊም ፈትል በመ​ጠ​ም​ጠ​ሚ​ያው ላይ በስ​ተ​ፊቱ ታን​ጠ​ለ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ ።


በላ​ዩም የተ​ጠ​ለ​ፈው የል​ብሰ መት​ከፍ ቋድ እንደ እርሱ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር አንድ ይሁን፤ ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀይ ግም​ጃም ከተ​ፈ​ተለ፥ ከጥሩ በፍ​ታም የተ​ሠራ ይሁን።


በመ​ቅ​ደስ ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል በብ​ል​ሃት የተ​ሠ​ሩ​ትን ልብ​ሶች፥ በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዘንድ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን የካ​ህ​ኑን የአ​ሮ​ንን ልብ​ሶች፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ልብ​ሶች አመጡ።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እነ​ር​ሱም በት​ው​ል​ዳ​ቸው ሁሉ በል​ብ​ሳ​ቸው ጫፍ ዘርፍ ያደ​ርጉ ዘንድ፥ በዘ​ር​ፉም ሁሉ ላይ ሰማ​ያዊ ፈትል ያደ​ርጉ ዘንድ እዘ​ዛ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos