Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 28:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የደረት ኪሱም በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ በላይ እንዲሆን ከኤፉዱም እንዳይለይ፥ የደረት ኪሱን ከቀለበቶቹ ወደ ኤፉዱ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል ያያይዙታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የደረት ኪሱም ቀለበቶች፣ የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ጋራ እንዳይላቀቅ፣ ከመታጠቂያው ጋራ በማገናኘት በሰማያዊ ገመድ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋራ ይያያዙ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በደረት ኪሱ ላይ ያሉትን ቀለበቶች በኤፉዱ ላይ ካሉት ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ድሪ እሰራቸው፤ በዚህ ዐይነት የደረት ኪሱ ከመታጠቂያው በላይ ስለሚሆን ልል አይሆንም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም በብ​ል​ሃት ከተ​ጠ​ለፈ ከል​ብሰ መት​ክፉ ቋድ በላይ እን​ዲ​ሆን፥ ከል​ብሰ መት​ከ​ፉም እን​ዳ​ይ​ለይ፥ ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከቀ​ለ​በ​ቶቹ ወደ ልብሰ መት​ከፉ ቀለ​በ​ቶች በሰ​ማ​ያዊ ፈትል ያያ​ይ​ዙ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የደረቱም ኪስ በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቍድ በላይ እንዲሆን ከኤፉዱም እንዳይለይ፥ የደረቱን ኪስ ከቀለበቶቹ ወደ ኤፉዱ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል ያስሩታል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 28:28
9 Referencias Cruzadas  

መረግድ፥ ለኤፉድና ለደረት ኪስ የሚደረግ ፈርጥ።


በተጨማሪም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፥ በኤፉዱም ፊት ለፊት ከትከሻዎቹ በታች በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቋድ በላይ በመያዣው አጠገብ ታደርጋቸዋለህ።


አሮንም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ ዘወትር መታሰቢያ እንዲሆን በጌታ ፊት የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርዱ ደረት ኪስ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸከም።


“የኤፉዱን መደረቢያ ሙሉ ሰማያዊ አድርገው።


በመጠምጠሚያው ፊት በሰማያዊ ፈትል በመጠምጠሚያው ላይ ስፋው።


በላዩ ያለው በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ መታጠቂያ ከእርሱ ጋር ወጥ ሆኖ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠራ ይሁን።


በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነትም እንዲያገለግሉበት የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶችና የልጆቹን ልብሶች አመጡ።


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ እነርሱም ትውልዶቻቸውም በልብሳቸው ጫፍ ዘርፍ እንዲያደርጉ፥ በዘርፉም ጫፍ ሁሉ ላይ ሰማያዊ ፈትል እንዲያኖሩበት እዘዛቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos