Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 34:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም፤ በአባቱ በዳዊት መንገድ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በጌታም ፊት ቅን ነገር አደረገ፥ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ኢዮስያስ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር አደረገ፤ የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም ምሳሌነት ከመከተል ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በእግዚአብሔርም ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም፥ ወደ ግራም አላለም።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 34:2
15 Referencias Cruzadas  

ከዳ​ዊ​ትም ቤት፤ መን​ግ​ሥ​ቱን ከፍዬ ሰጥ​ቼህ ነበር፤ ነገር ግን በፍ​ጹም ልቡ እንደ ተከ​ተ​ለኝ፥ በፊ​ቴም ቅን ነገር ብቻ እን​ዳ​ደ​ረገ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም እንደ ጠበቀ እንደ ባሪ​ያዬ እንደ ዳዊት አል​ሆ​ን​ህም።


ከኬ​ጥ​ያ​ዊው ከኦ​ርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘ​መኑ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አድ​ርጎ ነበ​ርና፥ ካዘ​ዘ​ውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላ​ለም ነበ​ርና።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ ቀኝም ግራም አላ​ለም።


አሳም በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ቅን ነገር አደ​ረገ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ ጋር ነበረ፤ በፊ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም በአ​ባቱ በዳ​ዊት መን​ገድ ሄዶ​አ​ልና፥ ጣዖ​ት​ንም አል​ፈ​ለ​ገ​ምና፤


ነገር ግን የአ​ባ​ቱን አም​ላክ ፈለገ፤ በአ​ባ​ቱም ትእ​ዛዝ ሄደ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሥራ አይ​ደ​ለም።


አባ​ቱም ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።


በነ​ገ​ሠም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ዓመት ገና ብላ​ቴና ሳለ የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን አም​ላክ ይፈ​ልግ ጀመረ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከኮ​ረ​ብ​ታ​ውና ከዐ​ፀ​ዶቹ፥ ከተ​ቀ​ረ​ጹ​ትና ቀል​ጠው ከተ​ሠ​ሩት ምስ​ሎች ያነጻ ጀመር።


ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤ እግርህንም ከመጥፎ መንገድ መልስ። እግዚአብሔር የቀኝ መንገዶችን ያውቃልና፥ የግራ መንገዶች ግን ጠማሞች ናቸው። እርሱም መሄጃህን የቀና ያደርጋል፥ አካሄድህንም በሰላም ያሳምራል።


እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ሩ​ህም ሕግ፥ እንደ ነገ​ሩ​ህም ፍርድ አድ​ርግ፤ ከነ​ገ​ሩህ ፍርድ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አት​በል።


ልቡ በወ​ን​ድ​ሞቹ ላይ እን​ዳ​ይ​ኰራ፥ የአ​ም​ላኩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እን​ዳ​ይ​ተው፥ ቀኝና ግራም እን​ዳ​ይል፥ እር​ሱም ልጆ​ቹም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ረዥም ዘመን ይገዙ ዘንድ።


ዛሬም ካዘ​ዝ​ሁህ ከእ​ነ​ዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ፥ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመ​ል​ካ​ቸ​ውም ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ባት​ከ​ተል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አም​ላ​ካ​ችሁ እን​ዳ​ዘ​ዛ​ችሁ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ከእ​ር​ሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አት​በሉ።


አገ​ል​ጋዬ ሙሴ እንደ አዘ​ዘህ ሕግን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ ጽና፤ እጅ​ግም በርታ፤ ሁሉን እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​ሠራ ታውቅ ዘንድ ከእ​ርሱ ወደ ቀኝ ወደ ግራም አት​በል።


በሙሴ ሕግ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ትጠ​ብ​ቁና ታደ​ርጉ ዘንድ በጣም በርቱ፥ ከእ​ር​ሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አት​በሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos