Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 4:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ ከቅጥሩ በስተኋላ በሚገኙ ግልጽ ቦታዎች ላይ ከሕዝቡ አንዳንዶቹ ሰይፋቸውን፣ ጦራቸውንና ቀስታቸውን እንደ ያዙ በየቤተ ሰባቸው በመመደብ ቦታቸውን እንዲይዙ አደረግሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 መኳንንቱን፥ ሹማምቱንና የቀሩትን ሕዝብ እንዲህ አልኋቸው፦ “ሥራው ብዙና ሰፊ ነው፥ እኛም በቅጥሩ ላይ አንዱ ከሌላው ርቆ ተለያይተናል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህም ከሕዝባችን መካከል ሰይፍ፥ ጦርና ቀስት የያዙ ሰዎችን በየጐሣቸው በማዘጋጀት፥ ሥራው ባልተጠናቀቀበት ቦታ ሁሉ በቅጽሩ ግንብ በስተጀርባ እንዲመሸጉ አደረግሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከቅ​ጥ​ሩም በስ​ተ​ኋላ በኩል ባለው በታ​ች​ኛው ክፍል በሰ​ዋራ ስፍራ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንና ጦራ​ቸ​ውን፥ ቀስ​ታ​ቸ​ው​ንም አስ​ይዤ ሕዝ​ቡን በየ​ወ​ገ​ና​ቸው አቆ​ም​ኋ​ቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ከቅጥሩም በስተ ኋላ በኩል ባለው በታችኛው ስፍራ ሰይፋቸውን ጦራቸውንም ቀስታቸውንም አስይዤ ሕዝቡን በየወገናቸው አቆምኋቸው።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 4:13
10 Referencias Cruzadas  

ከዚያም በአጠገባቸው የሚኖሩ አይሁድ መጥተው፣ “እናንተ የትም ቦታ ብትሆኑ፣ እኛን ማጥቃታቸው አይቀርም!” በማለት ዐሥር ጊዜ ደጋግመው ነገሩን።


እኔም፣ “ታላቅ ሥራ እየሠራሁ ስለ ሆነ፣ ወዳላችሁበት ስፍራ መውረድ አልችልም፤ ትቼው ወደ እናንተ ወርጄ ሥራው ለምን ይቆማል?” በማለት ይህን መልስ የሚያደርሱ መልእክተኞችን ወደ እነርሱ ላክሁ።


ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣ ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል።


“እንግዲህ፣ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልኆች እንደ ርግብ የዋሃን ሁኑ።


ወንድሞች ሆይ፤ በአስተሳሰባችሁ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፉ ነገር ሕፃናት ሁኑ፤ በአስተሳሰባችሁ ግን ጕልማሶች ሁኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos