Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሚክያስ 4:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 አሁን ግን ብዙ አሕዛብ፣ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል፤ እነርሱም፣ “የረከሰች ትሁን፤ ዐይናችንም ጽዮንን መዘባበቻ አድርጎ ይያት” ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አሁንም፦ “ትርከስ፥ ዓይናችን በጽዮን ላይ ይሁን” የሚሉ ብዙ አሕዛብ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አሁን ግን ብዙ ሕዝቦች በእናንተ ላይ ተሰብስበው እንዲህ ይላሉ፦ “ኢየሩሳሌም ትርከስ! እኛም መፍረስዋን እንይ!”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አሁንም፦ ርኩስ ትሁን፥ ዓይናችንም በጽዮን ላይ ይይ የሚሉ ብዙ አሕዛብ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 አሁንም፦ ርኩስ ትሁን፥ ዓይናችንም በጽዮን ላይ ይይ የሚሉ ብዙ አሕዛብ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል።

Ver Capítulo Copiar




ሚክያስ 4:11
15 Referencias Cruzadas  

ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።


በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ፤ በአንተም ላይ ተማማሉ፤


እርሱ ግን እንዲህ አላሰበም፤ በልቡም ይህ አልነበረም፤ ነገር ግን ዕቅዱ ለማጥፋት፣ ብዙ ሕዝቦችንም ለመደምሰስ ነበር።


ወዮ! የብዙ ሕዝቦች የቍጣ ድምፅ እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኻል! አቤት፤ የሰዎች ከፍተኛ ጩኸት እንደ ኀይለኛ ውሃ ያስገመግማል!


አርኤልን የሚወጋ የአሕዛብ ሁሉ መንጋ፣ በእርሷና በምሽጓ ላይ አደጋ የሚጥልና የሚከብባት፣ እንደ ሕልም በሌሊትም እንደሚታይ ራእይ ይሆናል።


ስለዚህ ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሰራዊቱን ሁሉ አስከትቶ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ፤ ከተማዪቱንም ከበቧት፤ በዙሪያውም የዐፈር ድልድል ሠሩ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ጢሮስ ሆይ፤ እነሆ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ባሕር ሞገዷን እንደምታስነሣ፣ ብዙ ሕዝብ አስነሣብሻለሁ።


“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በቀደመው ዘመን በባሪያዎቼ በእስራኤል ነቢያት ስለ እርሱ የተናገርሁለት ያ ሰው አንተ አይደለህምን? በዚያ ወቅት አንተን በእነርሱ ላይ እንደማመጣባቸው ለብዙ ዓመታት ትንቢት ተናገሩ።”


ክፉ ቀን በገጠመው ጊዜ፣ በወንድምህ ሥቃይ መደሰት አልነበረብህም፤ በጥፋታቸው ቀን፣ የይሁዳ ሕዝብ ሲያዝኑ ሐሤት ማድረግ አልነበረብህም፤ በጭንቀታቸውም ቀን፣ በትዕቢት ልትናገር አይገባህም ነበር።


ጠላቴም ታያለች፤ ኀፍረትንም ትከናነባለች፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ያለችኝን፣ ዐይኖቼ ውድቀቷን ያያሉ፤ አሁንም እንኳ፣ እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።


የምድር አሕዛብ ሁሉ በርሷ ላይ በሚሰበሰቡበት በዚያ ቀን፣ ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ የማይነቃነቅ ዐለት አደርጋታለሁ፤ ለማነቃነቅ የሚሞክሩ ሁሉ ራሳቸውን ይጐዳሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos