Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 51:58 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

58 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወፍራሙ የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል፤ ከፍ ያሉት ደጆቿም በእሳት ይቃጠላሉ፤ ሰዎቹ በከንቱ ይደክማሉ፤ የሕዝቡም ልፋት ለእሳት ይሆናል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

58 “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰፋፊዎቹ የባቢሎን ቅጥሮች ፈጽመው ይፈርሳሉ ረጃጅሞችም በሮችዋ በእሳት ይቃጠላሉ፤ ሕዝቡም በከንቱ ጉልበቱን ይፈስሳል፥ አሕዛብም የደከሙበት ነገር ለእሳት ይሆናል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

58 ሰፊው የባቢሎን ቅጽር ወድቆ ከመሬት ይደባለቃል፤ ከፍ ብለው የተሠሩ የቅጽር በሮችዋ በእሳት ይጋያሉ። የሕዝብዋ ድካም ከንቱ ይሆናል፤ ሕዝቦች የደከሙበት ነገር ሁሉ በእሳት ይወድማል። እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

58 የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሰፊው የባ​ቢ​ሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈ​ር​ሳል፤ ረጃ​ጅ​ሞች በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ ሕዝቡ ለከ​ንቱ ይደ​ክ​ማሉ፤ አሕ​ዛ​ብም በመ​ጀ​መ​ሪያ በእ​ሳት ያል​ቃሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

58 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰፊው የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል ረጃጅሞችም በሮችዋ በእሳት ይቃጠላሉ፥ የወገኖችም ድካም ከንቱ ትሆናለች፥ የአሕዛብም ሥራ ለእሳት ትሆናለች፥ እነርሱም ይደክማሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 51:58
13 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።


በተራቈተ ኰረብታ ዐናት ላይ ምልክት ስቀሉ፤ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ፤ በመሳፍንቱም በር እንዲገቡ፣ በእጅ ምልክት ስጡ።


የተቀበልሽው ምክር ሁሉ ድካም ብቻ ሆኖ አስቀርቶሻል! እነዚያ ከወር እስከ ወር ከዋክብትን አንጋጦ በማየት የሚተነብዩ፣ ኮከብ ቈጣሪዎች እስኪ ይምጡ፤ ከሚደርስብሽም ነገር እስኪ ያድኑሽ።


ድካማቸው በከንቱ አይቀርም፤ ዕድለ ቢስ ልጆችም አይወልዱም፤ እነርሱና ዘራቸው፣ እግዚአብሔር የባረከው ሕዝብ ይሆናሉ።


ከየአቅጣጫው ጩኹባት፤ እጇን ትሰጣለች፤ ምሽጓም ይወድቃል፤ ቅጥሮቿ ይፈርሳሉ። ይህ የእግዚአብሔር በቀል ነውና፣ እርሷን ተበቀሏት፤ በሌሎቹ ላይ እንዳደረገችውም አድርጉባት።


የባቢሎን ጦረኞች መዋጋት ትተዋል፤ በምሽጎቻቸው ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸው ተሟጥጧል፤ እንደ ሴት ሆነዋል፤ በማደሪያዎቿም እሳት ተለኵሷል፤ የደጇም መወርወሪያ ተሰብሯል።


ቤልን በባቢሎን ውስጥ እቀጣለሁ፤ የዋጠውን አስተፋዋለሁ፤ ሕዝቦች ከእንግዲህ ወደ እርሱ አይጐርፉም፤ የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል።


እንዲህም በል፤ ‘ባቢሎንም እኔ ከማመጣባት ጥፋት የተነሣ፣ እንደዚሁ ትሰጥማለች፤ ከእንግዲህም አትነሣም፤ ሕዝቧም ይወድቃል።’ ” የኤርምያስ ትንቢት እዚህ ላይ አበቃ።


“ ‘ባቢሎንን ለመፈወስ ሞክረን ነበር፤ እርሷ ግን ልትፈወስ አትችልም፤ ፍርዷ እስከ ሰማይ ስለ ደረሰ፣ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ስላለ፣ ትተናት ወደየአገራችን እንሂድ።’


ባልንጀራ ባልንጀራውን ያታልላል፤ እውነትን የሚናገር የለም፤ ሐሰትን ይናገሩ ዘንድ ምላሳቸውን አሠልጥነዋል፤ ኀጢአትንም በማድረግ ራሳቸውን አድክመዋል።


የሚያሳድዱን ከተረከዞቻችን ሥር ናቸው፤ ተጨንቀናል ዕረፍትም ዐጥተናል።


ሰዎች፣ ለእሳት ማገዶ እንዲሆን እንዲለፉ፣ ሕዝቦችም በከንቱ እንዲደክሙ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖ የለምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos