Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 36:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ወዳለው ወደ ጸሓፊው ክፍል ወረደ፤ በዚያም መኳንንቱ ሁሉ፦ ጸሓፊው ኤሊሳማ፣ የሸማያ ልጅ ድላያ፣ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፣ የሳፋን ልጅ ገማርያ፣ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ እንዲሁም ሌሎች መኳንንት ሁሉ ተቀምጠው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ወደ ንጉሡ ቤት ወደ ጸሐፊው ጓዳ ወረደ፤ እነሆም፥ አለቆች ሁሉ፥ ጸሐፊው ኤሊሳማ፥ የሸማያ ልጅ ድላያ፥ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፥ የሳፋን ልጅ ገማርያ፥ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ አለቆቹም ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እርሱም በቤተ መንግሥት ወደሚገኘው ባለሥልጣኖች ወደሚገኙበት ወደ ጸሐፊው ክፍል ሄደ፤ ጸሐፊው ኤሊሻማዕ፥ የሸማዕያ ልጅ ደላያ፥ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፥ የሳፋን ልጅ ገማርያ፥ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ ሌሎችም ባለ ሥልጣኖች እዚያ ተቀምጠው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ወደ ንጉ​ሡም ቤት ወደ ጸሓ​ፊው ክፍል ወረደ፤ እነ​ሆም አለ​ቆቹ ሁሉ፥ ጸሓ​ፊው ኤሊ​ሳማ፥ የሸ​ማያ ልጅ ድላያ፥ የዓ​ክ​ቦር ልጅ ኤል​ና​ታን፥ የሳ​ፋን ልጅ ገማ​ርያ፥ የሐ​ና​ንያ ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ፥ አለ​ቆ​ቹም ሁሉ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ወደ ንጉሡ ቤት ወደ ጸሐፊው ጓዳ ወረደ፥ እነሆም፥ አለቆች ሁሉ፥ ጸሐፊው ኤሊሳማ፥ የሸማያ ልጅ ድላያ፥ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፥ የሳፋን ልጅ ገማርያ፥ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ አለቆቹም ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 36:12
13 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ንጉሡ ካህኑን ኬልቅያስን፣ የሳፋን ልጅ አኪቃምን፣ የሚክያስን ልጅ ዓክቦርን፣ ጸሓፊውን ሳፋንንና የንጉሡን የቅርብ አገልጋይ ዓሳያን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤


ካህኑ ኬልቅያስ፣ አኪቃም፣ ዓክቦርና፣ ሳፋን፣ ዓሳያም የሐርሐስ የልጅ ልጅ፣ የቲቁዋ ልጅ የአልባሳት ጠባቂውን የሴሌምን ሚስት ነቢዪቱን ሕልዳናን ለመጠየቅ ሄዱ። እርሷም ምክር በጠየቋት ቦታ፣ ኢየሩሳሌም ውስጥ በሁለተኛው የከተማው ክፍል ትኖር ነበር።


በዘመነ መንግሥቱ በዐሥራ ስምንተኛውም ዓመት ኢዮስያስ የሜሶላምን የልጅ ልጅ የኤዜልያስን ልጅ ጸሓፊውን ሳፋንን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ላከው፤ እንዲህም አለው፤


ዮአኪን በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ወር ገዛ። እናቱ ኔስታ ትባላለች፤ እርሷም የኢየሩሳሌም ሰው የኤልናታን ልጅ ነበረች።


የይሁዳም ባለሥልጣኖች ስለ እነዚህ ነገሮች በሰሙ ጊዜ፣ ከቤተ መንግሥት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፤ በእግዚአብሔር ቤት፣ አዲሱ በር በተባለው መግቢያ ተቀመጡ።


ይሁን እንጂ ንጉሥ ኢዮአቄም የዓክቦርን ልጅ ኤልናታንንና ከርሱም ጋራ ሌሎችን ሰዎች ወደ ግብጽ ላካቸው፤


ነገር ግን የሳፋን ልጅ አኪቃም ከኤርምያስ ጐን ስለ ቆመ፣ ኤርምያስ ይገደል ዘንድ ለሕዝቡ ዐልፎ አልተሰጠም።


ኤልናታን፣ ድላያ፣ ገማርያም ንጉሡ ብራናውን እንዳያቃጥል ቢለምኑትም እንኳ አልሰማቸውም፣


መኳንንቱም ንጉሡን እንዲህ አሉት፤ “ይህ ሰው በሚናገረው ነገር በዚህች ከተማ የቀሩትን ወታደሮችና ሕዝቡንም ሁሉ ተስፋ የሚያስቈርጥ ስለ ሆነ መሞት አለበት፤ ይህ ሰው የሕዝቡን መጥፋት እንጂ መልካም ነገር አይሻም።”


ከንጉሣዊ ቤተ ሰብ የሆነው ከንጉሡ የጦር መኰንንኖች አንዱ የነበረው የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ በሰባተኛው ወር ከዐሥር ሰዎች ጋራ ወደ ምጽጳ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ፤ በዚያም በአንድነት ሊበሉ በማእድ ተቀምጠው ሳለ፣


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos