30 በጭቃ ውስጥ ሲጥመለመል ሹልና ስለ ታም የሆነው ቆዳው፥ እንደ ማረሻ ምድርን ይሰነጣጥቃል።
30 የሆዱ ሥር እንደ ሸካራ ገል ነው፤ እንደ መውቂያ መሣሪያም በጭቃ ላይ ምልክት ጥሎ ያልፋል።
እርሱ ዱላን የሚቈጥረው እንደ ሣር ነው፤ ሰዎችም ጦር ሲወረውሩበት በማፌዝ ይስቃል።
ባሕርን እንደ ፈላ ውሃ ያፍለቀልቀዋል፤ በማሰሮ ውስጥ እንደሚፈላ ዘይትም ያንተከትከዋል።
እነሆ፥ እኔ እንደ ስለታም፥ አዲስና፥ ጥርስ እንዳለው የመውቂያ መሣሪያ አደርግሃለሁ፤ ተራራዎችንም በማበራየት ታደቃቸዋለህ፤ ኰረብቶችንም ዳምጠህ እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።