Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 38:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ኢዮብ ሆይ! በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ከቶ ንጋትን አዘህ ታውቃለህን? ለንጋት ወገግታስ ቦታ መድበህለታልን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ከተወለድህ ጀምሮ ንጋትን አዝዘህ ታውቃለህን? ወይስ ወጋገን ስፍራውን እንዲይዝ አድርገሃል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በውኑ ከተወለድህ ጀምሮ ማለዳን አዝዘህ ታውቃለህን? ለወገግታም ስፍራውን አስታውቀኸዋልን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “የን​ጋት ወገ​ግታ በአ​ንተ ተፈ​ጥ​ሮ​አ​ልን? የአ​ጥ​ቢያ ኮከ​ብስ ትእ​ዛ​ዙን በአ​ንተ ዐው​ቋ​ልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12-13 የምድርን ዳርቻ ይይዝ ዘንድ፥ ከእርስዋም በደለኞች ይናወጡ ዘንድ፥ በውኑ ከተወለድህ ጀምሮ ማለዳን አዝዘሃልን? ለወገግታም ስፍራውን አስታውቀኸዋልን?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 38:12
14 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ብርሃኑን “ቀን” ብሎ ጠራው፤ ጨለማውንም “ሌሊት” ብሎ ሰየመው። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ ይህም አንድ ቀን ሆነ።


“ከሰው በፊት የተወለድክ አንተ ነህን? ተራራዎችስ ከመፈጠራቸው በፊት ተወልደህ ነበርን?


ሌቦች በሌሊት ቤት ሰርስረው ለስርቆት ይገባሉ፤ ቀን ግን ተሸሽገው ይውላሉ። ብርሃንንም ይጠላሉ።


እስከዚህ ድረስ ትመጣለህ! ከዚህም አታልፍም! የአንተም ብርቱ ማዕበል እዚህ ይቁም! ያልኩ እኔ ነኝ።


ንጋት በምድር ላይ ብርሃን እንዲያሳይ፥ ክፉ ሰዎችንም ከተደበቁበት ቦታ እንዲያጋልጥ ትእዛዝ ሰጥተህ ታውቃለህን?


ዓለም በተፈጠረ ጊዜ ተወልደህ ስለ ነበረ በእርግጥ ታውቃለህ! ዕድሜህም በጣም የገፋ ነው!


ለመሆኑ ዓለምን ስፈጥር አንተ በዚያ ነበርክን? የምታውቅና የምታስተውል ከሆነ እስቲ ንገረኝ።


የእኛ ዕድሜ ገና ትንሽ በመሆኑ ምንም አናውቅም፤ ዕድሜአችንም እንደ ጥላ የሚያልፍ ነው።


ቀኑንና ሌሊቱን የፈጠርክ፥ ፀሐይንና ጨረቃን በየቦታቸው ያጸናህ አንተ ነህ፤


“ፕሊያዲስ” የተባሉትን ሰባቱን ከዋክብትና “ኦርዮን” ተብለው የሚጠሩትን የከዋክብት ክምችትን የፈጠረ፥ ሌሊቱን ወደ ቀን፥ ቀኑንም ወደ ሌሊት የሚለውጥ፥ የባሕሩን ውሃ አዞ፥ በምድር ላይ እንዲፈስ የሚያደርግ፥ ኀያላንንና ምሽጎቻቸውን የሚደመስስ እርሱ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።


አምላካችን መሓሪና ርኅሩኅ በመሆኑ የደኅንነት ብርሃን ከወደላይ እንዲበራልን ያደርጋል።


ይህ ሁሉ ነቢያት የተናገሩት እውነት መሆኑን በበለጠ ያረጋግጡልናል፤ ስለዚህ በጨለማ ቦታ ለሚገኝ መብራት ትኲረት እንደምትሰጡ ነቢያት ለተናገሩት ትኲረት ስጡት፤ ይህንንም የምታደርጉት ጎሕ እስኪቀድና አጥቢያ ኮከብ በልባችሁ እስኪገለጥ ድረስ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos