Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 23:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 አንቺ የተረሳሽ ዘማዊት በገናሽን እየደረደርሽ በከተማ ውስጥ ዙሪ! እንዲያስታውሱሽ ጣዕመ ዜማ አሰሚ፤ ብዙ መዝሙሮችንም ዘምሪ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “አንች የተረሳሽ ጋለሞታ፤ በገና አንሺ፤ በከተማዪቱ ውስጥ ዙሪ፤ እንድትታወሺም፣ በገናሽን አሳምረሽ ምቺ፤ ብዙ ዘፈን ዝፈኚ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፥ መሰንቆ ያዢ በከተማ ላይም ዙሪ፤ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ ዘፈንሽንም አብዢ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 አንቺ የተ​ረ​ሳሽ ጋለ​ሞታ ሆይ፥ መሰ​ንቆ ያዢ፤ በከ​ተማ ላይም ዙሪ፤ መታ​ሰ​ቢ​ያም ይሆ​ን​ልሽ ዘንድ ዜማን አሳ​ምሪ፤ ዘፈ​ን​ሽ​ንም አብዢ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፥ መሰንቆ ያዢ በከተማ ላይም ዙሪ፥ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ ዘፈንሽንም አብዢ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 23:16
6 Referencias Cruzadas  

ጢሮስ ሰባ ዓመት ያኽል ተረስታ የምትኖርበት ጊዜ ይመጣል፤ ይህም የአንድ ንጉሥ ዕድሜ ነው፤ እነዚያ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ጢሮስ እንደ ዘማዊት ሴት እንዲህ ተብሎ ቅኔ የሚነገርባት ትሆናለች፦


ከሰባ ዓመት በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጐበኛታል፤ ወደ ቀድሞ የንግድ ሥራዋ እንድትመለስ ያደርጋታል፤ በምድር ላይ ከሚገኙ መንግሥታት ሁሉ ጋር ታመነዝራለች።


ወዳጆቻችሁ ሁሉ ረስተዋችኋል፤ እነርሱ እናንተን አይፈልጉአችሁም፤ ኃጢአታችሁ የበዛ፥ ክፋታችሁም እጅግ ከፍ ያለ ስለ ሆነ፥ እንደ ጠላት መታኋችሁ፤ ያለ ርኅራኄም ቀጣኋችሁ።


ዘፈንሽንና በበገና የምታሰሚውን የሙዚቃ ድምፅ ሁሉ ጸጥ አደርጋለሁ።


ይህም የሆነው ገደብ በሌለው የአምንዝራይቱ ፍትወት ምክንያት ነው፤ እርስዋ በመተት እመቤትነትና በቊንጅናዋ የምታታልልና መንግሥታትን በዝሙትዋ፥ ሕዝቦችን በጥንቈላዋ የምትማርክ ነች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos