Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 10:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 እነዚህ ሁሉ ሰዎች ባዕዳን ሴቶችን አግብተው የነበሩ ናቸው፤ እነርሱም ያገቡአቸውን ባዕዳን ሴቶች ሁሉ ፈተው ከነልጆቻቸው አባረሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 እነዚህ ሁሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ናቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ ከእነዚህ ሴቶች ልጆችን ወልደው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 እነዚህ ሁሉ እንግዶች ሚስቶችን አግብተው ነበር፤ ከእነዚህም አንዳንዶቹ ሚስቶች ልጆችን ወልደው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 እነ​ዚህ ሁሉ እን​ግ​ዶ​ቹን ሚስ​ቶች አግ​ብ​ተው ነበር፤ ከእ​ነ​ዚ​ህም ሚስ​ቶች ዐያ​ሌ​ዎቹ ልጆ​ችን ወል​ደው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 እነዚህ ሁሉ እንግዶቹን ሚስቶች አግብተው ነበር፤ ከእነዚህም ሚስቶች አያሌዎቹ ልጆችን ወልደው ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 10:44
6 Referencias Cruzadas  

ሰሎሞን ብዙ የባዕዳን አገሮችን ሴቶች አፈቀረ፤ በዚህም መሠረት ከግብጽ ንጉሥ ልጅ ሌላ የሒታውያን፥ የሞአባውያን፥ የዐሞናውያን፥ የኤዶማውያንና የሲዶናውያን ሴቶች ልጆችን አፈቀረ።


አሁን እንግዲህ እነዚህን ባዕዳን ሴቶች ከነልጆቻቸው ማሰናበት እንደሚገባን ለአምላካችን ቃል እንግባ፤ አንተ ጌታዬና የአምላካችንን ትእዛዝ የሚያከብሩ ሌሎችም የምትሰጡንን ምክር ሁሉ እንፈጽማለን፤ የእግዚአብሔር ሕግ የሚያዘውን ሁሉ እናደርጋለን፤


ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ሚስቶች የሚሆኑ ከእነዚያ ወገኖች አግብተዋል፤ አጋብተዋልም፤ ቅዱሱን ዘር ከሌሎች ከአካባቢው አሕዛብ ጋር ቀላቅለዋል፤ በዚህ እምነተ ቢስ በሆነ ተግባር መሪዎቹና ባለ ሥልጣኖቹ ግንባር ቀደም ሆነዋል።”


እንግዲህ እኔ የምልህን ብትሰማ በልዝብ አነጋገር ከምታጠምድ ከአመንዝራ ሴት ማምለጥ ትችላለህ።


ልጄ ሆይ! በአመንዝራይቱ ሴት ለምን ትማረካለህ? ለምንስ ከሌላው ሰው ሚስት ጋር ትባልጋለህ?


የአመንዝራ ሴት ከንፈር የማር ወለላ የሚያንጠባጥብ ይመስላል፤ ንግግርዋም ከዘይት ይልቅ የለዘበ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos