Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 28:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ሮማን የመሰለውና የወርቅ መርገፍ በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያውን ተከታትለው ይደረጋሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 የወርቅ ሻኵራዎቹና ሮማኖቹ በጨርቁ ጠርዝ ዙሪያ በመፈራረቅ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 የወርቅ ሻኩራና ሮማን፥ የወርቅ ሻኩራና ሮማን በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያውን ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 የወ​ርቅ ሻኩራ ሮማ​ንም፥ ሌላም የወ​ርቅ ሻኩራ ሮማ​ንም በቀ​ሚሱ ዘርፍ ዙሪ​ያ​ውን ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 የወርቅ ሻኵራ ሮማንም፥ ሌላም የወርቅ ሻኵራ ሮማንም በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያውን ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 28:34
15 Referencias Cruzadas  

ጌታ ሆይ! የምስጋና መዝሙር የሚያቀርቡልህና በቸርነትህ ብርሃን የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው።


በታችኛው ዘርፍ ዙሪያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ የተሠሩ የሮማን ፍሬ ቅርጽ አድርግበት፤ በፍሬዎቹ መካከል ጣልቃ የሚገቡ ከወርቅ የተሠሩ ትናንሽ ቃጭሎች አድርግበት።


አሮን በክህነት በሚያገለግልበት ጊዜ ይህን ቀሚስ ይልበስ፤ በተቀደሰው ስፍራ በፊቴ በተገኘ ጊዜ ወይም ከዚያ በሚወጣበት ጊዜ የመርገፉ ድምፅ ስለሚሰማ ከመሞት ይድናል።


የኤፉዱ መደረቢያ ቀሚስ የተሠራው ሙሉ በሙሉ ከሰማያዊ ከፈይ ነበር፤


እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት መርገፎቹ የሮማን ፍሬ፥ በልብሱ ግርጌ ዙሪያ አከታትለው አደረጉ።


ውዴ ከሌሎች ጐልማሶች ጋር ሲነጻጸር በዱር ዛፎች መካከል አምሮ እንደሚታይ የፖም ዛፍ ነው፤ እኔም እጅግ ደስ ብሎኝ በጥላው ሥር ዐረፍኩ፤ ጣፋጭ ፍሬውንም በመመገብ ተደሰትኩ።


የአንቺ መተላለፊያ በጣፋጭ ፍሬዎች እንደ ተሞላ እንደ ሮማን የአትክልት ቦታ ነው።


ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ያማሩ ናቸው፤ ስትነጋገሪም እጅግ ደስ ያሰኛሉ፤ ሁለቱ ጒንጮችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ዐይነ ርግብ ውስጥ ሲታዩ ለሁለት የተከፈለ የሮማን ፍንካች ይመስላሉ።


በሸለቆ የተተከሉትን ተክሎች ልምላሜ አይ ዘንድ ወይኑ አቈጥቊጦ፥ ሮማኑም አብቦ እንደ ሆነ ልመለከት ወደ ለውዝ ተክል ቦታ ወረድኩ፤


ሁለቱ ጒንጮችሽ በፊትሽ ዐይነ ርግብ ውስጥ ሲታዩ ለሁለት የተከፈሉ የሮማን ፍሬ ፍንካች ይመስላሉ።


ወደ ወላጅ እናቴ ቤት ባስገባሁህ ነበር፤ በዚያም ስለ ፍቅር ባስተማርከኝ ነበር፤ በሮማን ፍሬዬ ጭማቂ የጣፈጠውን መልካሙን የወይን ጠጅ ባጠጣሁህ ነበር።


እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።


እንዲሁም ለጌታ ተገቢ በሆነ መንገድ በመኖር እርሱን በፍጹም እንድታስደስቱ ማናቸውንም መልካም ሥራ በመሥራት ፍሬ እንድታፈሩና እግዚአብሔርንም በማወቅ እያደጋችሁ እንድትሄዱ እንጸልያለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos