Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 23:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “እናንተ በግብጽ ምድር መጻተኞች ስለ ነበራችሁ መጻተኛ ምን ዐይነት ሐዘን እንደሚደርስበት ታውቃላችሁና መጻተኛውን አታጒላሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “መጻተኛውን አትጨቍን፤ በግብጽ መጻተኛ ስለ ነበራችሁ፣ መጻተኛ ምን እንደሚሰማው እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 መጻተኛውን አትጨቁን፤ እናንተ ራሳችሁ በግብጽ ምድር መጻተኞች ስለ ነበራችሁ የመጻተኛ ነፍስ እንዴት እንደ ሆነች ታውቃላችሁና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በስ​ደ​ተ​ኛው ግፍ አታ​ድ​ርጉ፤ እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር ስደ​ተ​ኞች ስለ ነበ​ራ​ችሁ የስ​ደ​ተኛ ነፍስ እን​ዴት እንደ ሆነች ዐው​ቃ​ች​ኋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በስደተኛው ግፍ አታድርጉ፤ እናንተ በግብፅ ምድር ስደተኞች ስለ ነበራችሁ የስደተኛ ነፍስ እንዴት እንደ ሆነች አውቃችኋልና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 23:9
13 Referencias Cruzadas  

ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና አባትና እናት የሌላቸውን ልጆች ይገድላሉ፤ በምድራችን የሚኖሩትንም መጻተኞች ያጠፋሉ።


ነገር ግን ባሪያው በአንድ ቀን ወይም በሁለት ቀን ውስጥ ባይሞት አሳዳሪ ጌታው አይቀጣም፤ ባሪያውን ማጣቱ ራሱ ቅጣት ነው።


“ለእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ለሌላ ለማንኛውም አምላክ መሥዋዕት የሚያቀርብ በሞት ይቀጣ።


“እናንተም በግብጽ ምድር መጻተኞች ስለ ነበራችሁ መጻተኛውን በመጨቈን አታጒላሉ፤


የሀገሪቱ ሰዎች ዝርፊያና ቅሚያ ያካሄዳሉ፤ ድኾችን፥ ችግረኞችንና መጻተኞችን ፍትሕ በመንሣት ይበድላሉ።


በውስጥሽም አባትና እናት ይናቃሉ፤ የውጪ አገር ሰዎች ይታለላሉ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶችና አባትና እናት የሌላቸው ልጆች ይበደላሉ።


“በምድራችሁ ከእናንተ ጋር ባዕዳን ቢኖሩ አትበድሉአቸው፤


ታዲያ፥ እኔ ዕዳህን እንደ ተውኩልህ፥ አንተስ ባልንጀራህ ለሆነው አገልጋይ ዕዳውን ልትተውለት አይገባህም ነበርን?’


ስለዚህም እናንተም ለእነዚህ ስደተኞች ፍቅራችሁን ልታሳዩአቸው ይገባል፤ እናንተም ራሳችሁ በግብጽ ምድር መጻተኞች የሆናችሁበት ጊዜ ነበር።


“ኤዶማውያን ዘመዶችህ ስለ ሆኑ አትጸየፋቸው፤ በግብጽ ምድር ስደተኛ ሆነህ ስለ ኖርክ ግብጻውያንን አትጸየፋቸው።


“ ‘መብት በመግፈፍ መጻተኞችን፥ ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆችንና ባሎቻቸው የሞቱባቸው መበለቶችን የሚያንገላታ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos