Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 8:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሰሎሞን ለሚያከናውነው ልዩ ልዩ የሕንጻ ሥራ፥ የጒልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ገባሮች ሁለት መቶ ኀምሳ እስራኤላውያን ኀላፊዎች ነበሩአቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከእነዚህም ሁለት መቶ ዐምሳዎቹ የንጉሥ ሰሎሞን ሹማምት ሰዎቹን የሚቈጣጠሩ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እነዚህም በሕዝቡ ላይ ሥልጣን የነበራቸው የንጉሥ ሰሎሞን ከፍተኛ ሹማምት ሁለት መቶ ኀምሳ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እነ​ዚ​ህም በሕ​ዝቡ ላይ ያለ​ውን ሥራ የሚ​ቈ​ጣ​ጠሩ የን​ጉሡ የሰ​ሎ​ሞን ዓይ​ነ​ተ​ኞች አለ​ቆች ሁለት መቶ አምሳ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እነዚህም በሕዝቡ ላይ ሠልጥነው የነበሩ የንጉሡ የሰሎሞን ዓይነተኞች አለቆች ሁለት መቶ አምሳ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 8:10
5 Referencias Cruzadas  

የእነዚህ ሠራተኞች የበላይ ሆነው ሥራውን የሚቈጣጠሩ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሰዎችን አዘጋጀ፤


ሰሎሞን ለሚያከናውነው የሕንጻ ሥራ የጒልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ሰዎች አምስት መቶ ኀምሳ ኀላፊዎች ነበሩአቸው።


ከእነርሱም መካከል ሰባው ሺህ ዕቃ እንዲያጓጒዙ፥ ሰማኒያው ሺህ በተራራዎች ላይ ድንጋይ እንዲፈልጡ አደረገ፤ ደግሞም ሥራው በትክክል መካሄዱን የሚቈጣጠሩ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎችን ሾመ።


ሰሎሞን “የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ያለበት ስፍራ ሁሉ ቅዱስ ስለ ሆነ፥ ግብጻዊት ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤተ መንግሥት ውስጥ መኖር አይገባትም” በማለት የግብጽ ንጉሥ ልጅ የሆነችውን ሚስቱን ከዳዊት ከተማ አውጥቶ እርሱ ወዳሠራላት ወደ ሌላ መኖሪያ ቤት ተዘዋውራ እንድትኖር አደረገ።


ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ወገን ማንንም ባሪያ አድርጎ አላሠራም፤ እስራኤላውያን ወታደሮች፥ የጦር መኰንኖች፥ የጦር አዛዦች፥ ሠረገላ ለሚነዱ ሁሉ ኀላፊዎችና ፈረሰኞች ሆነው ያገለግሉ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos