Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 24:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ንጉሡና ካህኑ ዮዳሄ ገንዘቡን የቤተ መቅደሱ እድሳት ኀላፊዎች ለሆኑት ሰዎች ይሰጡአቸው ነበር፤ እነዚህም ኀላፊዎች ገንዘቡን ቤተ መቅደሱን የሚጠግኑ ግንበኞችን፥ አናጢዎችንና ብረታ ብረት ሠራተኞችን ይቀጥሩበት ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ንጉሡና ዮዳሄም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ እንዲያሠሩ ለተመደቡት ሰዎች ገንዘቡን አስረከቧቸው፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለማደስ ድንጋይ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችና ዐናጺዎችን እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለመጠገን የብረትና የናስ ሠራተኞችን ቀጠሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ንጉሡና ዮዳሄም በጌታ ቤት ሥራ ላይ ለተሾሙት ሰጡአቸው፤ እነርሱም የጌታን ቤት የሚጠግኑትን ጠራቢዎችንና አናጢዎችን፥ የጌታንም ቤት የሚያድሱትን የብረትና የናስ ሠራተኞችን ይቀጥሩበት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ንጉ​ሡና ኢዮ​አ​ዳም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ ላይ ለተ​ሾ​ሙት ሰጡ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የሚ​ጠ​ግ​ኑ​ትን ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንና አና​ጢ​ዎ​ችን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት የሚ​ያ​ድ​ሱ​ትን የብ​ረ​ትና የናስ ሠራ​ተ​ኞ​ችን ይቀ​ጥ​ሩ​በት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ንጉሡና ዮዳሄም በእግዚአብሔር ቤት ሥራ ላይ ለተሾሙት ሰጡአቸው፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠግኑትን ጠራቢዎችንና አናጢዎችን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት የሚያድሱትን የብረትና የናስ ሠራተኞችን ይገዙበት ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 24:12
7 Referencias Cruzadas  

የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት ይሠሩለት ዘንድ አናጢዎች፥ ግንበኞችና የሊባኖስ ዛፍ እንጨት አስይዞ መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ።


ንጉሥ ሰሎሞን በኮረብታማው አገር ድንጋይ የሚፈልጡ ሰማኒያ ሺህ፥ የተፈለጠውን ድንጋይ ተሸክመው የሚያመጡ ሰባ ሺህ ሰዎችን መደበ፤


ሌዋውያኑም ሣጥኑን ወስደው ኀላፊዎች ለሆኑት ለመንግሥት ባለሥልጣኖች በየቀኑ ያስረክቡት ነበር። ሣጥኑ በገንዘብ በሞላ ቊጥር የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊና የካህናት አለቃው እንደ ራሴ ገንዘቡን ከሣጥኑ አውጥተው ከወሰዱ በኋላ፥ ሣጥኑን መልሰው በቦታው ያኖሩት ነበር፤ በዚህ ዐይነት ብዙ ገንዘብ ሰበሰቡ።


ሠራተኞቹም በብርቱ ትጋት በመሥራት ቤተ መቅደሱን ቀድሞ በነበረው ሁኔታ በጥሩ አኳኋን አደሱት።


የኢዮአስ ልጆች ታሪክ፥ በኢዮአስ ላይ ተነግረው የነበሩት የትንቢት ቃላትና ኢዮአስ ቤተ መቅደሱን እንዴት እንዳደሰ በነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ መግለጫ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሜስያስ ነገሠ።


ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የአሕዛብን አምልኮ በማጥፋት ምድሪቱንና ቤተ መቅደሱን ካነጻ በኋላ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ያድሱ ዘንድ የአጻልያን ልጅ ሳፋንን፥ የኢየሩሳሌም አስተዳዳሪ የሆነውን ማዕሤያንና የኢዮአሐዝን ልጅ ጸሐፊውን ዮአሕን ላከ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos