2 ዜና መዋዕል 24:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ንጉሡና ዮዳሄም በጌታ ቤት ሥራ ላይ ለተሾሙት ሰጡአቸው፤ እነርሱም የጌታን ቤት የሚጠግኑትን ጠራቢዎችንና አናጢዎችን፥ የጌታንም ቤት የሚያድሱትን የብረትና የናስ ሠራተኞችን ይቀጥሩበት ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ንጉሡና ዮዳሄም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ እንዲያሠሩ ለተመደቡት ሰዎች ገንዘቡን አስረከቧቸው፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለማደስ ድንጋይ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችና ዐናጺዎችን እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለመጠገን የብረትና የናስ ሠራተኞችን ቀጠሩ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ንጉሡና ካህኑ ዮዳሄ ገንዘቡን የቤተ መቅደሱ እድሳት ኀላፊዎች ለሆኑት ሰዎች ይሰጡአቸው ነበር፤ እነዚህም ኀላፊዎች ገንዘቡን ቤተ መቅደሱን የሚጠግኑ ግንበኞችን፥ አናጢዎችንና ብረታ ብረት ሠራተኞችን ይቀጥሩበት ነበር፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ንጉሡና ኢዮአዳም በእግዚአብሔር ቤት ሥራ ላይ ለተሾሙት ሰጡአቸው፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠግኑትን ጠራቢዎችንና አናጢዎችን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት የሚያድሱትን የብረትና የናስ ሠራተኞችን ይቀጥሩበት ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ንጉሡና ዮዳሄም በእግዚአብሔር ቤት ሥራ ላይ ለተሾሙት ሰጡአቸው፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠግኑትን ጠራቢዎችንና አናጢዎችን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት የሚያድሱትን የብረትና የናስ ሠራተኞችን ይገዙበት ነበር። Ver Capítulo |