Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 21:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ኢዮአብም “ንጉሥ ሆይ፥ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ አሁን ካሉት ይልቅ በመቶ እጅ ያብዛልህ! እነርሱ በሙሉ የአንተ አገልጋዮች ናቸው፤ ታዲያ አንተ የሕዝብ ቈጠራ በማድረግ ሕዝቡን በሙሉ በደለኛ ለምን ታደርጋለህ?” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ኢዮአብ ግን፣ “እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት አሁን ካለው በላይ በመቶ ዕጥፍ ያብዛው፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ ሁሉስ ቢሆኑ የጌታዬ ተገዦች አይደሉምን? ታዲያ ንጉሡ ጌታዬ ይህን ማድረግ ለምን አስፈለገው? ለምንስ በእስራኤል ላይ በደል ያመጣል?” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ኢዮአብም አለ፦ “ጌታ ሕዝቡን በአሁኑ ላይ መቶ እጥፍ ይጨምር፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሁሉ የጌታዬ ባርያዎች አይደሉምን? ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል? በእስራኤል ላይ በደል ስለምን ያመጣል?”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ኢዮ​አ​ብም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ አሁን ባለ​በት መቶ እጥፍ ይጨ​ምር፤ የጌ​ታዬ የን​ጉሥ ዐይ​ኖ​ችም ይዩ፤ ሁሉም የጌ​ታዬ አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸው፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በደል ይሆን ዘንድ ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል?” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ኢዮአብም “እግዚአብሔር ሕዝቡን በአሁኑ ላይ መቶ እጥፍ ይጨምር፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሁሉ የጌታዬ ባሪያዎች አይደሉምን? ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል? በእስራኤል ላይ በደል ስለ ምን ያመጣል?” አለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 21:3
15 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ አቤሜሌክ አብርሃምን ጠርቶ፦ “ይህ ያደረግህብን ነገር ምንድን ነው? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ይህን በደል ያመጣህብን ምን ያስቀየምኩህ ነገር ቢኖር ነው? አንተ ያደረግህብኝን ነገር ከቶ ማንም ሰው አያደርገውም፤


ኢዮርብዓም ኃጢአት ስለሠራና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት ስለ መራ፥ እግዚአብሔር እስራኤልን ይተዋል።”


ስለዚህም ኢዮአስ ዮዳሄንና ሌሎቹንም ካህናት ወደ እርሱ ጠርቶ “ቤተ መቅደሱን ያላደሳችሁበት ምክንያት ምንድን ነው? ከዛሬ ጀምሮ የምትቀበሉትን ገንዘብ መያዝ የለባችሁም፤ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ይውል ዘንድ ገንዘቡን አስረክቡ” አላቸው።


እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተማዎች ስንል በርትተን እንዋጋ፤ ለዚህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን።”


ንጉሡ ግን ትእዛዙን እንዲፈጽም ኢዮአብን አስገደደው፤ ከዚህ በኋላ ኢዮአብ ከንጉሡ ፊት ወጣ፤ ሕዝቡንም ለመቊጠር በአገሪቱ በሙሉ ተዘዋውሮ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።


እግዚአብሔር እናንተና ልጆቻችሁ እንድትበዙ ያድርጋችሁ!


“የእስራኤልን ሕዝብ በምትቈጥርበት ጊዜ በሕዝብ ቈጠራው ወቅት መቅሠፍት እንዳይደርስባቸው እያንዳንዱ ሰው ለሕይወቱ ቤዛ የሚሆን ዋጋ ይክፈል።


አሮንንም “ከቶ ይህ ሕዝብ ምን አድርጎህ ነው ይህን የመሰለ አስከፊ ኃጢአት እንዲሠራ ያደረግኸው?” አለው።


የንጉሥ ታላቅነት የሚለካው በሚያስተዳድራቸው ሕዝብ ብዛት ነው፤ የሚገዛው ሕዝብ ከሌለው ግን ለንጉሡ ጥፋት ነው።


አምላክ ሆይ! የምድራችንን ወሰን በየአቅጣጫው በማስፋት መንግሥታችንን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ ሕዝባችንንም አበዛህ፤ ይህም አንተ የምትከብርበት ሆኖአል።


ሕዝባችሁም ባልተደመሰሰና ስማችሁም ባልተረሳ ነበር!”


አሁንም የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ሺህ ጊዜ እጥፍ በመጨመር ቊጥራችሁን አብዝቶ ያበልጽጋችሁ!


እነርሱም የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ የሚኖሩት የምናሴ ሕዝብ ወደሚኖሩባት ወደ ገለዓድ ምድር መጥተው እንዲህ አሉአቸው፦


ልጆቼ ሆይ! በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል ስለ እናንተ የተሠራጨው ወሬ መልካም አይደለምና እንዲህ ያለ ክፉ ነገር አታድርጉ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos