Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 39:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ይህም የሚሆነው ከአሕዛብ በመለስኋቸው ጊዜ፥ ከጠላቶቻቸውም ምድር በሰበሰብኋቸው ጊዜ በብዙ አሕዛብም ፊት በእነሱ በተቀደስሁ ጊዜ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ከአሕዛብ ምድር መልሼ ሳመጣቸው፣ ከጠላቶቻቸው አገር ስሰበስባቸው የራሴን ቅድስና በእነርሱ በኩል በብዙ ሕዝቦች ፊት አሳያለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እነርሱን ከሕዝቦች መካከል ስመልሳቸውና ከጠላቶቻቸው አገሮችም ብዙ ሕዝቦች እያዩ ስሰበስባቸው በእነርሱ አማካይነት ቅድስናዬን እገልጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ከአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ በመ​ለ​ስ​ኋ​ቸው ጊዜ፥ ከአ​ሕ​ዛ​ብም ሀገ​ሮች በሰ​በ​ሰ​ብ​ኋ​ቸው ጊዜ፥ በብዙ አሕ​ዛ​ብም ፊት በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ባ​ቸው ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 39:27
12 Referencias Cruzadas  

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍትሕ ከፍ ከፍ ይላል፤ ቅዱሱም አምላክ ቅድስናውን በጽድቅ ይገልጻል።


ከአሕዛብም ዘንድ ባወጣኋችሁ ጊዜ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በሰበሰብኋችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀበላችኋለሁ፥ በአሕዛብም ፊት እቀደስባችኋለሁ።


አንተም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የእስራኤልን ልጆች ከሄዱባቸው ሕዝቦች መካከል እወስዳለሁ፥ ከየስፍራውም እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ።


ምድርን እንደሚሸፍን ደመና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትወጣለህ። ጎግ ሆይ፥ በአንተ በኩል ቅድስናዬን በፊታቸው በምገልጥበት ጊዜ፥ አሕዛብ እንዲያውቁኝ፥ በኋለኛው ዘመን በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።


ታላቅ እሆናለሁ፥ እቀደሳለሁም፥ በብዙ አሕዛብ ዐይን የታወቅሁ እሆናለሁ፥ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ከብዙ ዘመንም በኋላ ትፈለጋለህ፤ በኋለኛውም ዘመን፥ የዘለዓለም ባድማ በነበሩ በእስራኤል ተራሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰበሰበች፥ ከሰይፍ ወደ ተመለሰች ምድር ትገባለህ፤ እርሷም ከሕዝብ ውስጥ ወጥታለች ሁሉም ሳይፈሩ ይቀመጡባታል።


የምድሪቱ ሕዝቦች ሁሉ ይቀብሩአቸዋል፤ በምከበርበት ቀን፥ ለሥም ይሆንላቸዋል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አሁን የያዕቆብን ምርኮ እመልሳለሁ ለእስራኤልም ቤት ሁሉ እራራለሁ፥ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀናለሁ።


እኔ ጌታ አምላካቸው እንደሆንሁ ያውቃሉ፥ በአሕዛብ እንዲማረኩ አድርጌአቸዋለሁና፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም ሰብስቤአቸዋለሁና፥ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ በዚያ አላስቀርም።


ሙሴም አሮንን፦ “ጌታ፦ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ዝም አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos