ሕዝቅኤል 39:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ማንም ሳያስፈራቸው በምድራቸው በሰላም በተቀመጡ ጊዜ፥ እፍረታቸውንና የበደሉኝን በደላቸውን ይሸከማሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 የሚያስፈራቸው ማንም ሳይኖር በምድራቸው ያለ ሥጋት በሚኖሩበት ጊዜ፣ ውርደታቸውንና ለእኔ ባለ መታመን የኖሩበትን ዘመን ይረሳሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 የሚያስፈራቸው ነገር ሳይኖር በገዛ ምድራቸው በሰላም ይኖሩ በነበረ ጊዜ የፈጸሙትን አሳፋሪ ተግባርና ለእኔ አለመታመናቸውን ሁሉ ይረሳሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 በምድራቸው ተዘልለው በተቀመጡ ጊዜ እፍረታቸውንና የበደሉኝን በደላቸውን ሁሉ ይሸከማሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26-27 ማንም ሳያስፈራቸው በምድራቸው ተዘልለው በተቀመጡ ጊዜ ከአሕዛብም ዘንድ በመለስኋቸው ጊዜ ከጠላቶቻቸውም ምድር በሰበሰብኋቸው ጊዜ በብዙ አሕዛብም ፊት በተቀደስሁባቸው ጊዜ፥ እፍረታቸውንና የበደሉኝን በደላቸውን ሁሉ ይሸከማሉ። Ver Capítulo |