Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 5:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እርግማንንም የሚያመጣ ይህ ውኃ ወደ ሆድሽ ይግባ፥ ሆድሽንም ይንፋው፥ ጭንሽንም ያበስብሰው ይላታል፤ ሴቲቱም፦ አሜን አሜን ትላለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ይህን ርግማን የሚያመጣ ውሃ በጠጣሽ ጊዜም ሆድሽን ያሳብጠው፤ ጭንሽን ያስልለው።” “ ‘ሴትዮዋም፣ “አሜን፤ አሜን” ትበል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እርግማንንም የሚያመጣው ይህ ውኃ ወደ ሆድሽ ይግባ፥ ሆድሽንም ይንፋው፥ ጭንሽንም ያሰልስለው፤’ ሴቲቱም፦ ‘አሜን አሜን’ ትላለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ይህም ውሃ ወደ ሰውነትሽ ገብቶ ሆድሽን ያሳብጠው፤ ማሕፀንሽንም ያኰማትረው።’ ሴትዮዋም ‘አሜን፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ያድርግብኝ’ ብላ ትመልሳለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ርግ​ማ​ን​ንም የሚ​ያ​መጣ ይህ ውኃ ወደ ሆድሽ ይግባ፥ ማኅ​ፀ​ን​ሽ​ንም ይሰ​ን​ጥ​ቀው፤ ጎን​ሽም ይር​ገፍ። ሴቲ​ቱም፦ ይሁን ይሁን ትላ​ለች።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 5:22
16 Referencias Cruzadas  

እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ አፍህ ይብላ፥ በምሰጥህም በዚህ መጽሐፍ ሆድህን ሙላ አለኝ። እኔም በላሁት፥ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠ።


ካህኑም እነዚህን መርገሞች በሰሌዳ ይጽፈዋል፥ በመራራውም ውኃ ይደመስሰዋል፤


ውኃውን ካጠጣት በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ ረክሳና በባልዋ ላይ አመንዝራ እንደ ሆነች፥ እርግማንን የሚያመጣው ውኃ ገብቶ መራራ ይሆንባታል፥ ሆድዋም ይነፋል፥ ጭንዋም ይሰለስላል፤ ሴቲቱም በሕዝብዋ መካከል ለመርገም ትሆናለች።


እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም።


ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።


ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos