Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 27:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ባየሃትም ጊዜ ወንድምህ አሮን እንደ ተከማቸ አንተ ደግሞ ወደ ወገንህ ትከማቻለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ካየኸውም በኋላ አንተም እንደ ወንድምህ እንደ አሮን ወደ ሕዝብህ ትሰበሰባለህ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ባየሃትም ጊዜ ወንድምህ አሮን እንደ ተከማቸ አንተ ደግሞ ወደ ወገንህ ትከማቻለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እርሱንም ካየህ በኋላ ወንድምህ አሮን እንደ ሞተ አንተም ትሞታለህ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ባየ​ሃ​ትም ጊዜ ወን​ድ​ምህ አሮን በሖር ተራራ እንደ ተጨ​መረ አንተ ደግሞ ወደ ወገ​ንህ ትጨ​መ​ራ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 27:13
11 Referencias Cruzadas  

እስማኤልም የኖረበት የዕድሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው፤ ነፍሱን ሰጠ ሞትንም፤ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ።


አብርሃናም ነፍሱን ሰጠ በመልካም ሽምግልናም ሞተ ሸመገለ፥ ብዙ ዘመንም ጠገበ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ።


ስለ እስራኤል ልጆች በቀል ምድያማውያንን ተበቀል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ወገኖችህ ትከማቻለህ።


ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።


እግዚአብሔርም ደግሞ በእናንተ ምክንያት በእኔ ተቆጣ እንዲህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደዚያ አትገባም፤


የእስራኤልም ልጆች ከብኤሮት ብኔያዕቃን ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ በዚያም አሮን ሞተ በዚያም ተቀበረ፤ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ።


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የምትሞትበት ቀን፥ እነሆ፥ ቀረበ፤ ኢያሱን ጠርተህ እርሱን አዝዘው ዘንድ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከእርሱ ጋር ቁም አለው። ሙሴና ኢያሱም ሄደው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ቆሙ።


እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ትተኛለህ፤ ይህም ሕዝብ ይነሣል፥ ይቀመጥባትም ዘንድ በሚሄድባት ምድር መካከል ያሉትን ሌሎችን አማልክት ተከትሎ ያመነዝራል፥ እኔንም ይተወኛል፥ ከእነርሱም ጋር ያደርግሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ።


ወንድምህም አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ ወደ ወገኖቹም እንደ ተከማቸ፥ በወጣህበት ተራራ ሙት፥ ወደ ወገኖችህም ተከማች፤


እኔ ግን በዚህች ምድር እሞታለሁ፥ ዮርዳኖስንም አልሻገርም፤ እናንተ ግን ትሻገራላችሁ፥ ያችንም መልካሚቱን ምድር ትወርሳላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos