Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 14:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፥ ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፦ ለአምላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የይሁዳም ሰዎች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ከዚያም የቄኔዛዊው የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ ስለ አንተና ስለ እኔ፣ የእግዚአብሔር ሰው ለሆነው ለሙሴ የተናገረውን ታውቃለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ “ለእግዚአብሔር ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ ጌታ በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አንድ ቀን ከይሁዳ ነገድ የሆኑ ሰዎች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ከእነርሱ አንዱ የቀኒዛዊው የይፉኔ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ “በቃዴስ በርኔ በነበርንበት ጊዜ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ስለ አንተና ስለ እኔ የተናገረውን ታውቃለህ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የይ​ሁ​ዳም ልጆች በጌ​ል​ገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔ​ዛ​ዊ​ውም የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፥ “ለአ​ም​ላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃ​ዴስ በርኔ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታው​ቃ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 14:6
30 Referencias Cruzadas  

ኢዮርብዓምም ዕጣን እያጠነ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ፥ እነሆም፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በእግዚአብሔር ቃል ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤


ከእግዚአብሔርም ሰው በኋላ ሄደ፤ በአድባርም ዛፍ በታች ተቀምጦ አገኘውና “ከይሁዳ የመጣህ የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” አለው። እርሱም “እኔ ነኝ፤” አለ።


እርሱም “በሚመጣው ዓመት በዚህ ወራት ወንድ ልጅ ትታቀፊአለሽ፤” አለ፤ እርስዋም “አይደለም፤ ጌታዬ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ባሪያህን እንዳትዋሻት እለምንሃለሁ፤” አለች።


አንድ ሰውም ከበኣልሻሊሻ የበኵራቱን እንጀራ፥ ሃያ የገብስ እንጀራ፥ የእህልም እሸት በአቁማዳ ይዞ ወደ እግዚአብሔር ሰው መጣ፤ እርሱም “ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ስጣቸው፤” አለ።


ለባልዋም “ይህ በእኛ ዘንድ ሁልጊዜ የሚያልፈው ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆነ አውቃለሁ።


እስኪያፍርም ድረስ ትኵር ብሎ ተመለከተው፤ የእግዚአብሔርም ሰው አነባ።


ኤልሳዕም ወደ ደማስቆ መጣ፤ የሶርያም ንጉሥ ቤንሀዳድ ታምሞ ነበር፤ ወሬኞችም “የእግዚአብሔር ሰው ወደዚህ መጥቶአል፤” ብለው ነገሩት።


የእግዚአብሔርም ሰው የሙሴ ልጆች በሌዊ ነገድ ተቈጠሩ።


ወደ እግዚአብሔርም ቤት በበረኛው በሰሎም ልጅ በመዕሤያ ጓዳ በላይ ባለው በአለቆች ጓዳ አጠገብ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ጌዴልያ ልጅ ወደ ሐናን ልጆች ጓዳ አገባኋቸው።


በፋራን ምድረ በዳና በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ሄደው ደረሱ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።


ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና፦ ማሸነፍ እንችላለንንና እንውጣ፥ እንውረሰው አለ።


ከይሁዳ ነገድ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፤


ባሪያዬ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ ከእርሱ ጋር ስለ ሆነ ፈጽሞም ስለተከተለኝ እርሱ ወደ ገባባት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል።


ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር በእርስዋ አስቀምጣችሁ ዘንድ እጄን ዘርግቼ ወደ ማልሁላችሁ ምድር በእውነት እናንተ አትገቡም።


ምድርን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤


እግዚአብሔር ስለ እነርሱ፦ በእውነት በምድረ በዳ ይሞታሉ ብሎ ተናግሮአልና። ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ ከነዌም ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ አንድ ሰው ስንኳ አልቀረም።


የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ሳይሞት የእስራኤልን ልጆች የባረከባት በረከት ይህች ናት።


እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሣም፤


የእግዚአብሔር ባሪያም ሙሴ እንደ እግዚአብሔር ቃል በዚያ በሞዓብ ምድር ሞተ።


አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።


ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ወደ ሰፈሩ ወደ ጌልገላ ተመለሱ።


ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ስለ ተከተለ ኬብሮን እስከ ዛሬ ለቄኔዛዊው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆነች።


የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፥ ልጁንም ዓክሳን አጋባው።


ሕዝቡም በመጀመሪያው ወር በአሥረኛው ቀን ከዮርዳኖስ ወጡ፥ በኢያሪኮም ዳርቻ በምሥራቅ በኩል በጌልገላ ሰፈሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos