Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 14:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበረ፥ ነገር ግን በመካከላቸው ለሌዋውያን ርስት አልሰጣቸውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሙሴ ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው፣ የዮርዳኖስን ምሥራቅ ክፍል ርስት አድርጎ ሰጣቸው፤ ሌዋውያኑ ግን ዐብረዋቸው እንዲካፈሉ አላደረገም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበረ፤ ነገር ግን በመካከላቸው ለሌዋውያን ርስት አልሰጣቸውም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን ምድር ለሁለት ተኩል ነገዶች ርስት አድርጎ ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለሌዋውያን ግን በእነርሱ መካከል ርስት አልሰጣቸውም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ለሁ​ለቱ ነገ​ድና ለእ​ኩ​ሌ​ታው ነገድ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ርስት አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 14:3
9 Referencias Cruzadas  

ርስትም አድርጋችሁ ምድርን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድር የተቀደሰውን የዕጣ ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ እግዚአብሔር ታቀርባላችሁ። ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል፥ በዳርቻው ሁሉ ዙሪያውን የተቀደሰ ይሆናል።


የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና የእስራኤል ልጆች መቱአቸው፥ የእግዚአብሔርም ባሪያ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።


ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አልሰጠም፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የቀረበው በእሳት የተደረገ መሥዋዕት ርስታቸው ነው፥ እርሱ እንደ ተናገራቸው።


ድንበራቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ በሸለቆው መካከል ያለችው ከተማ፥ የሜድባ ሜዳ ሁሉ፥


ሐሴቦንም፥ በሜዳውም ያሉት ከተሞችዋ ሁሉ፥ ዲቦን፥ ባሞትበኣል፥


የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንደ ሰጣቸው ከእርሱ ከምናሴ ጋር የሮቤልና የጋድ ልጆች በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀበሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos