La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መዝሙር 43

የስደት ጊዜ ጸሎት

1 አምላክ ሆይ! ፍረድልኝ፤ በአንተ ከማያምኑ አሕዛብ ፊት ስለ እኔ ተከራከርልኝ፤ ከአታላዮችና ከክፉ ሰዎችም እጅ አድነኝ።

2 አንተ አምላኬ፥ ጠንካራ ምሽጌ ነህ፤ ታዲያ፥ ስለምን ትተወኛለህ? ለምንስ ጠላቶቼ እያበሳጩ ያሳዝኑኝ?

3 ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ እየመሩ ወደ ተቀደሰው ተራራህ፥ ወደ ማደሪያ መቅደስህም ያምጡኝ።

4 አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።

5 እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ? ለምንስ እጨነቃለሁ? በእግዚአብሔር እተማመናለሁ። ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia