La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መዝሙር 20

ድል ለማግኘት የቀረበ ጸሎት

1 በችግር ቀን እግዚአብሔር ጸሎትህን ይስማ! የያዕቆብ አምላክም ስም ይጠብቅህ!

2 ከመቅደሱ ርዳታውን ይላክልህ፤ ከጽዮን ተራራም ይደግፍህ።

3 መባህን ሁሉ ይቀበልልህ፤ በመሥዋዕትህም ደስ ይበለው።

4 የልብህን ምኞት ይስጥህ፤ ሐሳብህን ሁሉ ይፈጽምልህ፤

5 ድል በማድረግህ እልል እንላለን፤ በአምላካችንም ስም ዓርማችንን ከፍ እናደርጋለን፤ እግዚአብሔር ልመናህን ሁሉ ይፈጽምልህ።

6 እግዚአብሔር ቀብቶ ያነገሠውን እንደሚረዳ አሁን ዐውቃለሁ፤ በቀኝ እጁ ታላቅ ድልን በማቀዳጀት ከተቀደሰው ቦታ ከሰማይ ለጸሎቱ መልስ ይሰጠዋል።

7 አንዳንዶች በጦር ሠረገሎቻቸው፥ ሌሎችም በፈረሶቻቸው ይመካሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ኀይል እንታመናለን።

8 እነርሱ ተሰናክለው ይወድቃሉ፤ እኛ ግን እንነሣለን፤ ጸንተንም እንቆማለን።

9 አምላክ ሆይ! ንጉሡን ከጠላቶቹ እጅ አድነው፤ እኛም በምንጠራህ ጊዜ ስማን።

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia