La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 120 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መዝሙር 120

ከሐሰተኞችና ከአታላዮች ለመዳን የሚቀርብ ጸሎት

1 መከራ በደረሰብኝ ጊዜ፥ ወደ እግዚአብሔር ጮኽኩ፤ እርሱም ሰማኝ።

2 እግዚአብሔር ሆይ! ከሐሰተኞችና ከአታላዮች አድነኝ።

3 እናንተ አታላዮች! እግዚአብሔር እናንተን ምን ቢያደርጋችሁ ይሻላል? እንዴትስ ቢቀጣችሁ ይሻላል?

4 በተሳለ የወታደር ፍላጻ ይወጋችኋል፤ በከሰል ፍምም ያቃጥላችኋል።

5 በቄዳር ሕዝብ መካከል በሜሼክ ስደተኛ ሆኜ በመኖሬ ወዮልኝ!

6 ሰላምን ከሚጠሉ ሕዝቦች ጋር እጅግ ለረጅም ጊዜ ኖርኩ።

7 እኔ ሰላምን እደግፋለሁ፤ ስለ ሰላም በምናገርበት ጊዜ እነርሱ ስለ ጦርነት ያወራሉ።

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia