መዝሙር 132 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መዝሙር 132የመዓርግ መዝሙር።1 ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው። 2 ከራሱ ጀምሮ እስከ ጢሙ፥ በልብሱ መደረቢያ ላይ፥ እስከሚወርደው እስከ አሮን ጢም ድረስ እንደሚፈስ ሽቱ ነው። 3 በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔምም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለም አዝዞአልና። |