ዘካርያስ 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተመልሼም ዓይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አንድ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አየሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገናም ተመለከትሁ፤ በዚያም በፊቴ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተመልሼም ዐይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አንድ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አየሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም ስመለከት አንድ የተጠቀለለ መጽሐፍ በአየር ላይ ሲበር አየሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመልሼም ዓይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አንድ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አየሁ። |
የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፤ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።