ስማችንም በጊዜ ይዘነጋል፤ ሥራችንንም የሚያስበው ማንም የለም፤ ሕይወታችንም እንደ ደመና ፍለጋ ያልፋል፤ እንደ ጉምም ይበተናል፤ በፀሐይ ጨረር እንደ ተበተነ፥ በሙቀቱም እንደ ቀለጠ ውርጭ ይሆናል።
ከጊዜ በኋላም ስማችን ይረሳል፤ የሠራነውንም የሚያስታውስ አይኖርም፤ ሕይወታችንም እንደ ደመና ነጠብጣብ የልፋል፤ የፀሐይ ጨረር እንዳባረረው፥ ሙቀቷ እንደገፈፈው ጉም ሟሙቶ ይቀራል።