የተገዛልህ ሁሉ ደመወዝ ባንተ ዘንድ አይደር፤ በጊዜው ስጠው እንጂ። ለእግዚአብሔር ብትገዛ ዋጋህ ይበዛልሃልና፤ ራስህን ዕወቅ፤ በሥራህና በጠባይህ ሁሉ ጠቢብ ሁን።
የሰሩልህን ሰዎች ደሞዝ በፍጥነት ከፈል እንጂ ለነገ አታሳድር። እግዚአብሔርን ካገለገልክ ዋጋህን ይከፍልሃል። ልጄ ሆይ በሥራህ ሁሉ ተጠንቀቅ፥ በጠባይህም ሁሉ ሥነ-ሥርዓት ያለህ ሁን።