ሰሎሞንም እንደ አባቶቹ አረፈ ከእርሱም በኋላ አእምሮ የሌለው ልጁን ለእስራኤል ተወ። ይኸውም ሕዝቡን በምክሩ ያሳመፃቸው ሮብዓም ነው። እስራኤልን ያሳታቸው፥ ለኤፍሬምም የኀጢአት መንገድን ያሳየ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ነበረ።
ሰሎሞን ከአባቶቹ ጐን አረፈ፥ ዙፋኑን ለልጆቹ አንዱ፥ ከሕዝቡ መካከል እጅግ የማይረባው፥ ማስተዋል የጐደለውና ሕዝቡንም ለዓመፅ የገፋፋው ሮብዓም ወረሰ።