በልቡናቸውም ጥበብን ያሳድርባቸው ዘንድ፥ በዘመናቸው ሁሉ ክብራቸውና በረከታቸው እንዳይጠፋባቸው፥ ወገኖቹንም በእውነት ይገዟቸው ዘንድ ከልጆቹ ጋራ ለእርሱ ክህነት ርስቱ ነው።
የአባቶቻችሁ ደግነት እንዳይጠፋ፥ ወገኖቻቸውም ክብራቸውን እንዳወርሱ፥ ሕዝቡን በትክክል ታስተዳድሩ ዘንድ፥ እግዚአብሔር ልባችሁን በጥበብ ይሙላው።