የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም በክብር ሦስተኛ ነው፤ ለአምልኮተ እግዚአብሔር ቀንቶአልና፥ ሕዝቡንም ለማስተማር አስነሥቶታልና፥ በልቡናው ቸርነትም ከእግዚአብሔር ፈቃድ የተነሣ ለእስራኤል አስተሰረየ።
ጌታን በመፍራት ትጋቱ፥ ሕዝቡ ባመፀ ወቅት በእምነቱ በመጽናቱ፥ በልበ ሙሉነትና በድፍረት በመቆሙ፥ ለእሥራኤልም ስርየትን በማስገኘቱ፥ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ ክብርን በተመለከተ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ነው።