የጠላት መዘባበቻ፥ በከተማም መነጋገሪያ፥ በሕዝቡም መካከል መሰደቢያ እንዳታደርግህ፥ በብዙ ሰዎች ፊትም እንዳታሳፍርህ የማታፍር ልጅን አጽንተህ ጠብቃት።
ልጅህ አስቸጋሪ ነችን? የጠላቶችህ መሳቂያ፥ የከተማው መዘባበቻ፥ የወሬኞች መጠቋቆሚያ እንዳታደርግህ፥ በሕዝብም ፊት ኀፍረትን እንዳታከናንብህ በብርቱ ጠብቃት።