ሩት 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፋሬስም ትውልድ ይህ ነው፣ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ የፋሬስ ቤተ ሰብ ትውልድ ይህ ነው፦ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፋሬስም ትውልድ ይህ ነው፥ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፋሬስ አንሥቶ እስከ ዳዊት ያለው የትውልድ ሐረግ የሚከተለው ነው፤ ፋሬስ ሔጽሮንን ወለደ፤ ሔጽሮን አራምን ወለደ፤ አራም ዐሚናዳብን ወለደ፤ ዐሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ እሴይም ዳዊትን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፋሬስም ትውልድ ይህ ነው፤ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፤ |
ሴቶችም ጎረቤቶችዋ፥ ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት እያሉ ስም አወጡለት፣ ስሙንም ኢዮቤድ ብለው ጠሩት። እርሱም የዳዊት አባት የእሴይ አባት ነው።